ጲላጦስም የለመኑት ይሆንላቸው ዘንድ ፈረደበት።
ስለዚህ ጲላጦስ የጠየቁት እንዲፈጸም ውሳኔ አስተላለፈ።
ጲላጦስም ልመናቸው እንዲፈጸም ፈረደበት።
በዚህም ምክንያት የጠየቁት እንዲደረግላቸው ጲላጦስ ፈረደ።
ጲላጦስም ልመናቸው እንዲሆንላቸው ፈረደበት።
ለዐመፅ ከብዙ ሰው ጋር አንድ አትሁን፤ ፍርድንም ለማጣመም ከብዙ ሰው ጋር አትጨመር።
ኃጥኡን ጻድቅ፥ ጻድቁንም ኃጥእ ብሎ መፍረድ በእግዚአብሔር ዘንድ የረከሰና የተናቀ ነው።
በዚያን ጊዜ በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን ገርፎ ሊሰቀል አሳልፎ ሰጠ።
ጲላጦስም የሕዝቡን ፈቃድ ሊያደርግ ወዶ በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስንም ገርፎ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠ።
እንዲሰቅሉትም ቃላቸውን ከፍ አድርገው እየጮሁ ለመኑ፤ ጩኸታቸውና የካህናት አለቆች ድምፅም በረታ።
ያን የለመኑትን፥ ነፍስ በመግደልና ሁከት በማድረግ የታሰረውንም ሰው ፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን ለፈቃዳቸው አሳልፎ ሰጣቸው።
ከዚህም በኋላ ጲላጦስ ጌታችን ኢየሱስን ይዞ ገረፈው።