ሉቃስ 15:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተነሥቶም ወደ አባቱ ሄደ፤ አባቱም ከሩቅ አየውና ራራለት፤ ሮጦም አንገቱን አቅፎ ሳመው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም ተነሥቶ ወደ አባቱ ሄደ። “ነገር ግን፣ እርሱ ገና ሩቅ ሳለ፣ አባቱ አይቶት ራራለት፤ ወደ እርሱም እየሮጠ ሄዶ ዐቅፎ ሳመው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተነሥቶም ወደ አባቱ መጣ። እርሱም ገና ሩቅ ሳለ አባቱ አየውና አዘነለት፤ ሮጦም አንገቱን አቀፈውና ሳመው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ተነሥቶ ወደ አባቱ ሄደ። “አባቱም ገና በሩቅ ሳለ ልጁን አየው፤ ራርቶለትም ወደ እርሱ ሮጠ፤ ዕቅፍ አድርጎም ሳመው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተነሥቶም ወደ አባቱ መጣ። እርሱም ገና ሩቅ ሳለ አባቱ አየውና አዘነለት፥ ሮጦም አንገቱን አቀፈውና ሳመው። |
ዮሴፍም ሰረገላውን አዘጋጀ፤ አባቱንም እስራኤልን ሊገናኘው ወደ ኤሮስ ከተማ ወጣ፤ በአየውም ጊዜ አንገቱን አቀፈው፤ ረዥም ጊዜም አለቀሰ።
ኢዮአብም ወደ ንጉሥ መጥቶ ነገረው፤ አቤሴሎምንም ጠራው፥ ወደ ንጉሡም ገብቶ ሰገደለት፤ በንጉሡም ፊት ወደ ምድር በግንባሩ ወደቀ፤ ንጉሡም አቤሴሎምን ሳመው።
“በውኑ ሴት፥ ልጅዋን ትረሳለችን? ከማኅፀንዋ ለተወለደውስ አትራራምን? ሴት ይህን ብትረሳ፥ እኔ አንቺን አልረሳሽም።
በእውነት ኤፍሬም ለእኔ የተወደደ ልጅ ነው፤ ደስ የሚያሰኝም ሕፃን ነው፤ በእርሱ ላይ በተናገርሁ ቍጥር አስበዋለሁ፤ ስለዚህ አንጀቴ ታወከችለት፤ ርኅራኄም እራራለታለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር።
እኔም “አምልኮቴን ትተሃል አልሁ፤ ኤፍሬም ሆይ! እንዴት አደርግሃለሁ? እስራኤል ሆይ! እንዴትስ እደግፍሃለሁ? እንዴትስ አደርግሃለሁ? እንደ አዳማ ነውን? ወይስ እንደ ሲባዮ? ልቤ በውስጤ ተናውጣለች፤ ምሕረቴም ተገልጣለች።
ልጁም፦ ‘አባቴ ሆይ፥ በሰማይም፥ በፊትህም በደልሁ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅህ ልባል አይገባኝም፤ ነገር ግን ከአገልጋዮችህ እንደ አንዱ አድርገኝ’ አለው።