Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ሳሙኤል 14:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ኢዮ​አ​ብም ወደ ንጉሥ መጥቶ ነገ​ረው፤ አቤ​ሴ​ሎ​ም​ንም ጠራው፥ ወደ ንጉ​ሡም ገብቶ ሰገ​ደ​ለት፤ በን​ጉ​ሡም ፊት ወደ ምድር በግ​ን​ባሩ ወደቀ፤ ንጉ​ሡም አቤ​ሴ​ሎ​ምን ሳመው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ኢዮአብም ወደ ንጉሡ ሄዶ ይህንኑ ነገረው። ከዚያም ንጉሡ አቤሴሎምን አስጠራው፤ እርሱም መጥቶ በንጉሡ ፊት በግምባሩ ተደፍቶ እጅ ነሣ፤ ንጉሡም አቤሴሎምን ሳመው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ኢዮአብም ወደ ንጉሡ ሄዶ ነገረው። ከዚያም ንጉሡ አቤሴሎምን አስጠራው፤ እርሱም መጥቶ በንጉሡ ፊት በግምባሩ ተደፍቶ እጅ ነሣ፤ ንጉሡም አቤሴሎምን ሳመው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ስለዚህም ኢዮአብ ወደ ንጉሥ ዳዊት ሄደና አቤሴሎም ያለውን ሁሉ ነገረው፤ ንጉሡም አቤሴሎምን አስጠራ፤ አቤሴሎምም ሄዶ በንጉሡ ፊት ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ ነሣ፤ ንጉሡም ሳመው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ኢዮአብም ወደ ንጉሥ መጥቶ ነገረው፥ አቤሴሎምንም ጠራው፥ ወደ ንጉሡም ገብቶ በንጉሥ ፊት ወደ ምድር በግምባሩ ተደፋ፥ ንጉሡም አቤሴሎምን ሳመው።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 14:33
7 Referencias Cruzadas  

ተነ​ሥ​ቶም ወደ አባቱ ሄደ፤ አባ​ቱም ከሩቅ አየ​ውና ራራ​ለት፤ ሮጦም አን​ገ​ቱን አቅፎ ሳመው።


ዔሳ​ውም ሊገ​ና​ኘው ሮጠ፤ አን​ገ​ቱ​ንም አቅፎ ሳመው፤ ሁለ​ቱም በአ​ን​ድ​ነት አለ​ቀሱ።


ወን​ድ​ሞ​ቹን ሁሉ ሳማ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ አለ​ቀሰ፤ ከዚ​ያም በኋላ ወን​ድ​ሞቹ ከእ​ርሱ ጋር ተጨ​ዋ​ወቱ።


አባቱ ይስ​ሐ​ቅም፥ “ልጄ ሆይ፥ ወደ እኔ ቅረብ፤ ሳመ​ኝም” አለው።


ሰውም እጅ ለመ​ን​ሣት ወደ እርሱ በቀ​ረበ ጊዜ እጁን ዘር​ግቶ አቅፎ ይስ​መው ነበር።


ሕዝ​ቡም ሁሉ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገሩ፤ ንጉ​ሡም ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገረ፤ ንጉ​ሡም ቤር​ዜ​ሊን አቅፎ ሳመው፤ መረ​ቀ​ውም፤ ወደ ስፍ​ራ​ውም ተመ​ለሰ።


ንጉሡ ሰሎ​ሞ​ንም ላከ፤ ከመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም አወ​ረ​ዱት፤ መጥ​ቶም ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን ሰገደ፤ ሰሎ​ሞ​ንም፥ “ወደ ቤትህ ሂድ” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios