አሁንም አቤቱ፥ የጻድቃን አምላካቸው አንተ ነህ። ንስሓን የፈጠርህ ለጻድቅ ሰው አይደለምና፥ አንተን ላልበደሉ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም አይደለምና፤ ነገር ግን የእኔን የኃጥኡን ንስሓ ወደ ማየት ተመለስ።
ሉቃስ 15:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተነሥቼ ወደ አባቴ ልሂድና እንዲህ ልበለው፦ ‘አባቴ ሆይ፥ በሰማይም፥ በፊትህም በደልሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተነሥቼ ወደ አባቴ ልሂድና፣ እንዲህ ልበለው፤ አባቴ ሆይ፤ በሰማይና በአንተ ፊት በድያለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተነሥቼም ወደ አባቴ እሄዳለሁና “አባቴ ሆይ! በሰማይና በፊትህ በደልሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተነሥቼ ወደ አባቴ ልሂድና፦ አባባ፥ በእግዚአብሔርና በአንተ ፊት በድያለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተነሥቼም ወደ አባቴ እሄዳለሁና፦ አባቴ ሆይ፥ በሰማይና በፊትህ በደልሁ፥ |
አሁንም አቤቱ፥ የጻድቃን አምላካቸው አንተ ነህ። ንስሓን የፈጠርህ ለጻድቅ ሰው አይደለምና፥ አንተን ላልበደሉ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም አይደለምና፤ ነገር ግን የእኔን የኃጥኡን ንስሓ ወደ ማየት ተመለስ።
አንተ አባታችን ነህ፤ አብርሃም ግን አላወቀንም፤ እስራኤልም አልተገነዘበንም፤ ነገር ግን አንተ አባታችን አድነን፤ ስምህም ለዘለዓለም በእኛ ላይ ነው።
“እኔም፦ ይሁን አልሁ፤ በወንዶች ልጆች መካከል እሾምሃለሁ፤ አሕዛብን የሚገዛ ሁሉን ቻይ የሆነ የእግዚአብሔርን ርስት የተመረጠችውን ምድር ለአንተ እሰጥሃለሁ፤ አባቴ ትለኛለህ፤ ከእኔም አትመለስም አልሁ ብለሃልና።
በእውነት ኤፍሬም ለእኔ የተወደደ ልጅ ነው፤ ደስ የሚያሰኝም ሕፃን ነው፤ በእርሱ ላይ በተናገርሁ ቍጥር አስበዋለሁ፤ ስለዚህ አንጀቴ ታወከችለት፤ ርኅራኄም እራራለታለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር።
እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው!
እርሱም እንዲህ አላቸው፥ “በምትጸልዩበት ጊዜ እንዲህ በሉ፦ በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፥ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነ እንዲሁም በምድር ይሁን።
ልጁም፦ ‘አባቴ ሆይ፥ በሰማይም፥ በፊትህም በደልሁ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅህ ልባል አይገባኝም፤ ነገር ግን ከአገልጋዮችህ እንደ አንዱ አድርገኝ’ አለው።
ቀራጩ ግን ራቅ ብሎ ቆመ፤ ዐይኖቹንም ወደ ላይ ወደ ሰማይ ሊያነሣ አልወደደም፤ ደረቱንም እየመታ፦ ‘አቤቱ፥ እኔን ኀጢኣተኛውን ይቅር በለኝ’ አለ።