Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 15:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ተነሥቼም ወደ አባቴ እሄዳለሁና “አባቴ ሆይ! በሰማይና በፊትህ በደልሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ተነሥቼ ወደ አባቴ ልሂድና፣ እንዲህ ልበለው፤ አባቴ ሆይ፤ በሰማይና በአንተ ፊት በድያለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ተነሥቼ ወደ አባቴ ልሂድና፦ አባባ፥ በእግዚአብሔርና በአንተ ፊት በድያለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ተነ​ሥቼ ወደ አባቴ ልሂ​ድና እን​ዲህ ልበ​ለው፦ ‘አባቴ ሆይ፥ በሰ​ማ​ይም፥ በፊ​ት​ህም በደ​ልሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ተነሥቼም ወደ አባቴ እሄዳለሁና፦ አባቴ ሆይ፥ በሰማይና በፊትህ በደልሁ፥

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 15:18
36 Referencias Cruzadas  

ኖን። መንገዳችንን እንመርምርና እንፈትን፥ ወደ እግዚአብሔርም እንመለስ።


ልጁም ‘አባቴ ሆይ! በሰማይና በፊትህ በደልሁ፤ ወደፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም፤’ አለው።


ቀራጩ ግን በሩቅ ቆሞ ዐይኖቹን ወደ ሰማይ ሊያነሣ እንኳን አልፈለገም፤ ነገር ግን ‘አምላክ ሆይ! እኔን ኀጢአተኛውን ማረኝ፤’ እያለ ደረቱን ይመታ ነበር።


የሰዎችን በደል ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ ይቅር ይላችኋል፤


እኔ ግን፦ “‘ከወንዶች ልጆች ጋር እንዴት አስቀምጥሻለሁ? ያማረችውንስ ምድር እጅግ የከበረችውን የአሕዛብን ርስት እንዴት እሰጥሻለሁ? ብዬ ነበር። ደግሞ፦ አባቴ ብለሽ ትጠሪኛለሽ፤ እኔንም ከመከተል አትመለሽም ብዬ ነበር።


አቤቱ፥ በደሌ ብዙ ነውና ስለ ስምህ ይቅር በለኝ።


ስለዚህ እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ፦ ‘በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ! ስምህ ይቀደስ፤


ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ በእርሱ ይጠመቁ ነበር።


በእውነት ኤፍሬም የተወደደ ልጄ ነውን? ወይስ ደስ የምሰኝበት ሕፃን ነውን? በእርሱ ላይ በተናገርሁ ቍጥር አሁንም ድረስ በትክክል አስታውሰዋለሁ፤ ስለዚህ አንጀቴ ታወከችለት ርኅራኄም እራራለታለሁ፥ ይላል ጌታ።


አብርሃም ባያውቀን፥ እስራኤልም ባይገነዘበን አንተ አባታችን ነህ፤ አቤቱ ጌታ አንተ አባታችን ነህ፤ ስምህም ከዘለዓለም ታዳጊያችን ነው።


ልጅን ከመቅጣት ቸል አትበል፥ በበትር ብትመታው አይሞትምና።


እንግዲህ እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳለ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁማ ለሚለምኑት መልካም ነገርን እንዴት አብልጦ አይሰጣቸውም!


ደግሞም ጸሎቱ፥ ጌታም እንደ ተለመነው፥ ኃጢአቱና መተላለፉ ሁሉ፥ ራሱንም ሳያዋርድ የኮረብታው መስገጃዎችን የሠራበት የማምለኪያ ዐፀዱንና የተቀረጹትንም ምስሎች የተከለበት ስፍራ፥ እነሆ፥ በባለ ራእዮቹ ታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል።


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “በማናቸውም ጊዜ ስትጸልዩ እንዲህ በሉ፦ ‘በሰማያት የምትኖር አባት ሆይ! ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤


እኛ እንዳንጠፋ፥ እግዚአብሔር ራርቶ ከሚነደው ቁጣው ይመለስ እንደሆነ ማን ያውቃል?


ወደ ጥልቁ ወደ ባሕሩ ልብ ጣልኸኝ፥ ወንዝም ከበበኝ፥ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ ላይ አለፉ።


ተስፋ የሆነው እንደሆነ አፉን በአፈር ውስጥ ያኑር።


ወደ ልቡም ተመልሶ እንዲህ አለ ‘ምግብ የሚተርፋቸው የአባቴ ተቀጣሪዎች ስንት ናቸው? እኔ ግን ከዚህ በራብ እጠፋለሁ።


ወደፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም፤ ከተቀጣሪዎችህ እንደ አንዱ አድርገኝ፤”’ እለዋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios