እነሆ፥ ባሪያህ በፊትህ ምሕረትን አግኝቼ እንደሆነ፥ ሰውነቴንም ታድናት ዘንድ፥ ቸርነትህን አብዝተህልኝ እንደ ሆነ፥ መከራ አግኝቶኝ እንዳልጠፋ ወደ ተራራ ሸሽቼ ራሴን ማዳን አልችልም።
ሉቃስ 1:58 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘመዶችዋና ጎረቤቶችዋም እግዚአብሔር ቸርነቱን እንዳበዛላት በሰሙ ጊዜ ከእርስዋ ጋር ደስ አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጎረቤቶቿና ዘመዶቿም ጌታ ታላቅ ምሕረት እንዳደረገላት ሰሙ፤ የደስታዋም ተካፋዮች ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጎረቤቶችዋም ዘመዶችዋም ጌታ ታላቅ ምሕረቱን እንዳደረገላት ሰምተው ከእርሷ ጋር ደስ አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጐረቤቶችዋና ዘመዶችዋ ሁሉ ጌታ ታላቅ ምሕረቱን እንዳደረገላት ሰምተው ከእርስዋ ጋር ተደሰቱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጎረቤቶችዋም ዘመዶችዋም ጌታ ምሕረቱን እንዳገነነላት ሰምተው ከእርስዋ ጋር ደስ አላቸው። |
እነሆ፥ ባሪያህ በፊትህ ምሕረትን አግኝቼ እንደሆነ፥ ሰውነቴንም ታድናት ዘንድ፥ ቸርነትህን አብዝተህልኝ እንደ ሆነ፥ መከራ አግኝቶኝ እንዳልጠፋ ወደ ተራራ ሸሽቼ ራሴን ማዳን አልችልም።
የጠራውንም እንዲህ አለው፥ “በበዓል ምሳ ወይም ራት በምታደርግበት ጊዜ ወዳጆችህንና ወንድሞችህን፥ ዘመዶችህንና ጎረቤቶችህን፥ ባለጸጎች ባልንጀሮችህንም አትጥራ፤ እነርሱም ይጠሩሃልና፤ ብድርም ይሆንብሃልና።
አንዱ የአካል ክፍል ቢታመም ከእርሱ ጋር የአካል ክፍሎች ሁሉ ይታመማሉ፤ አንዱ የአካል ክፍል ደስ ቢለውም የአካል ክፍሎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል።