Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 21:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ሣራም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ አሰ​ኘኝ፤ ይህን የሚ​ሰማ ሁሉ በእኔ ምክ​ን​ያት ደስ ይሰ​ኛ​ልና” አለች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ሣራም፣ “እግዚአብሔር ሣቅ አድሎኛል፤ ስለዚህ፣ ይህን የሚሰማ ሁሉ ከእኔ ጋራ ይሥቃል” አለች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ሣራም፦ “እግዚአብሔር ሳቅ አድርጎልኛል፥ ይህንንም የሚሰማ ሁሉ በእኔ ምክንያት ይስቃል” አለች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ሣራ “እግዚአብሔር ደስታና ሳቅ አመጣልኝ፤ ስለዚህ ይህን ነገር የሚሰማ ሁሉ ከእኔ ጋር ይስቃል” አለች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ሣራም እግዚአብሔር ሳቅ አድርጎልኛል፤ ይህንንም የሚሰማ ሁሉ በእኔ ምክንያት ይስቃል አለች።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 21:6
17 Referencias Cruzadas  

አብ​ር​ሃ​ምም በግ​ን​ባሩ ወደቀ፤ ሳቀም፤ በል​ቡም እን​ዲህ ብሎ አሰበ፥ “የመቶ ዓመት ሰው ስሆን በውኑ እኔ ልጅ እወ​ል​ዳ​ለ​ሁን? ዘጠና ዓመት የሆ​ና​ትም ሣራ ትወ​ል​ዳ​ለ​ችን?”


ለእኛ አይ​ደ​ለም፥ አቤቱ፥ ለእኛ አይ​ደ​ለም፥ ነገር ግን ለስ​ምህ፥ ስለ ምሕ​ረ​ት​ህና ስለ እው​ነ​ት​ህም ምስ​ጋ​ናን እን​ስጥ


በማ​ለዳ መገ​ሥ​ገ​ሣ​ች​ሁም ከንቱ ነው። ለወ​ዳ​ጆቹ እን​ቅ​ል​ፍን በሰጠ ጊዜ፥ እና​ንተ የመ​ከ​ራን እን​ጀራ የም​ት​በሉ፥ ከተ​ቀ​መ​ጣ​ች​ሁ​በት ተነሡ።


“በውኑ ሴት፥ ልጅ​ዋን ትረ​ሳ​ለ​ችን? ከማ​ኅ​ፀ​ንዋ ለተ​ወ​ለ​ደ​ውስ አት​ራ​ራ​ምን? ሴት ይህን ብት​ረሳ፥ እኔ አን​ቺን አል​ረ​ሳ​ሽም።


አን​ቺም በል​ብሽ፦ የወ​ላድ መካን ሆኛ​ለ​ሁና፥ እኔም መበ​ለት ነኝና እነ​ዚ​ህን ማን ወለ​ደ​ልኝ? እነ​ዚ​ህ​ንስ ማን አሳ​ደ​ጋ​ቸው? እነሆ፥ ብቻ​ዬን ቀርቼ ነበር፤ እነ​ዚ​ህስ ከወ​ዴት መጡ?” ትያ​ለሽ።


አንቺ ያል​ወ​ለ​ድሽ መካን ሆይ፥ ደስ ይበ​ልሽ፤ አንቺ ያላ​ማ​ጥሽ ሆይ፥ እልል በዪ፤ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆ​ነ​ቺቱ ልጆች በዝ​ተ​ዋ​ልና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ወንድ ልጅ ተወ​ል​ዶ​ል​ሃል ብሎ ለአ​ባቴ የም​ሥ​ራች ነግሮ ደስ ያሰ​ኘው ሰው የተ​ረ​ገመ ይሁን።


ደስ​ታና ሐሤ​ትም ይሆ​ን​ል​ሃል፤ በመ​ወ​ለ​ዱም ብዙ​ዎች ደስ ይላ​ቸ​ዋል።


ዘመ​ዶ​ች​ዋና ጎረ​ቤ​ቶ​ች​ዋም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር​ነ​ቱን እን​ዳ​በ​ዛ​ላት በሰሙ ጊዜ ከእ​ር​ስዋ ጋር ደስ አላ​ቸው።


ደስ ከሚ​ለው ጋር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ከሚ​ያ​ለ​ቅ​ሰው ጋርም አል​ቅሱ።


ራስዋ ሳራም መካን ሳለች ባረ​ጀ​ች​በት ወራት ዘር ታስ​ገኝ ዘንድ በእ​ም​ነት ኀይ​ልን አገ​ኘች፤ ተስፋ የሰ​ጣት የታ​መነ እንደ ሆነ አም​ና​ለ​ችና።


እር​ስ​ዋም አለች፥ “ጌታዬ ሆይ! በሕ​ያው ነፍ​ስህ እም​ላ​ለሁ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመ​ጸ​ለይ በዚህ በፊ​ትህ ቆማ የነ​በ​ረች ሴት እኔ ነኝ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos