La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 9:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሙሴም ያዘ​ዛ​ቸ​ውን ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ አመጡ፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ ቀር​በው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቆሙ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነርሱም ሙሴ ያዘዛቸውን ሁሉ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ አመጡ፤ ሕዝቡም በሙሉ ቀርበው በእግዚአብሔር ፊት ቆሙ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሙሴም ያዘዛቸውን ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ አመጡ፤ ማኅበሩም ሁሉ ቀርበው በጌታ ፊት ቆሙ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነርሱም ሙሴ ያዘዛቸውን ሁሉ ወደ ድንኳኑ ፊት ለፊት አመጡ፤ ማኅበሩም ሁሉ ለእግዚአብሔር ለመስገድ ወደዚያ ተጠግተው ቆሙ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሙሴም ያዘዛቸውን ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ አመጡ፤ ማኅበሩም ሁሉ ቀርበው በእግዚአብሔር ፊት ቆሙ።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 9:5
7 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትም ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ላት ስፍራ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ያመጣ ዘንድ እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሰበ​ሰበ።


ሰባ​ተ​ኛ​ውም ወር በደ​ረሰ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ነበሩ። ሕዝ​ቡም ሁሉ በው​ኃው በር ፊት ወዳ​ለው አደ​ባ​ባይ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰ​በ​ሰቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለእ​ስ​ራ​ኤል ያዘ​ዘ​ውን የሙ​ሴን ሕግ መጽ​ሐፍ ያመጣ ዘንድ ጸሓ​ፊ​ውን ዕዝ​ራን ነገ​ሩት።


ሙሴም ሕዝ​ቡን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ለማ​ገ​ና​ኘት ከሰ​ፈር አወ​ጣ​ቸው፤ በተ​ራ​ራ​ውም እግ​ርጌ ቆሙ።


ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት በሬ​ንና አውራ በግን፥ በዘ​ይ​ትም የተ​ለ​ወሰ የእ​ህ​ልን ቍር​ባን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይሠዉ ዘንድ ውሰዱ፤ ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይገ​ለ​ጥ​ላ​ች​ኋ​ልና ብለህ ንገ​ራ​ቸው።”


ሙሴም፥ “ታደ​ር​ጉት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዛ​ችሁ ቃል ይህ ነው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ይገ​ለ​ጥ​ላ​ች​ኋል” አለ።


ይሰ​ሙና ይማሩ ዘንድ፥ አም​ላ​ካ​ች​ሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈሩ ዘንድ፥ የዚ​ህን ሕግ ቃሎች ሁሉ ሰም​ተው ያደ​ርጉ ዘንድ ሕዝ​ቡን ወን​ዶ​ችና ሴቶ​ችን፥ ሕፃ​ኖ​ቻ​ች​ሁ​ንም፥ በሀ​ገ​ራ​ችሁ ደጅ ያለ​ው​ንም መጻ​ተኛ ሰብ​ስብ።