Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 19:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ሙሴም ሕዝ​ቡን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ለማ​ገ​ና​ኘት ከሰ​ፈር አወ​ጣ​ቸው፤ በተ​ራ​ራ​ውም እግ​ርጌ ቆሙ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ከዚያም ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋራ ለማገናኘት ሕዝቡን ከሰፈር ይዞ ወጣ፤ ከተራራውም ግርጌ ቆሙ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ሙሴም ሕዝቡን ከእግዚአብሔር ጋር ለማገናኘት ከሰፈር አወጣቸው፤ በተራራው እግርጌ ቆሙ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ሙሴም ከሰፈር እየመራ አውጥቶ ወደ እግዚአብሔር አቀረባቸው፤ እነርሱም በተራራው እግር ሥር ቆሙ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ሙሴም ሕዝቡን ከእግዚአብሔር ጋር ለማገናኘት ከሰፈር አወጣቸው፤ ከተራራውም እግርጌ ቆሙ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 19:17
8 Referencias Cruzadas  

የማ​ንም እጅ አይ​ንካ፤ የሚ​ነ​ካ​ውም ሁሉ በድ​ን​ጋይ ይወ​ገ​ራል፤ ወይም በፍ​ላጻ ይወ​ጋል፤ እን​ስሳ ወይም ሰው ቢሆን የቀ​ረበ አይ​ድ​ንም። የመ​ለ​ከት ድም​ፅና ደመና በተ​ራ​ራው በዐ​ለፈ ጊዜ ወደ ተራ​ራው ይውጡ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን በማ​ለዳ ጊዜ ነጐ​ድ​ጓ​ድና መብ​ረቅ፥ ከባ​ድም ደመና፥ ጉምም በሲና ተራራ ላይ ሆነ፤ እጅ​ግም የበ​ረታ የቀ​ንደ መለ​ከት ድምፅ ተሰማ፤ በሰ​ፈ​ሩም የነ​በ​ሩት ሕዝብ ሁሉ ተን​ቀ​ጠ​ቀጡ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ሳት ስለ ወረ​ደ​በት የሲና ተራራ ሁሉ እንደ ምድጃ ጢስ ይጤስ ነበር፤ ከእ​ር​ሱም እንደ እቶን ጢስ ያለ ጢስ ይወጣ ነበር፤ ተራ​ራ​ውም ሁሉ እጅግ ይና​ወጥ ነበር፤ ሕዝ​ቡም ፈጽ​መው ደነ​ገጡ።


ሙሴም ያዘ​ዛ​ቸ​ውን ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ አመጡ፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ ቀር​በው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቆሙ።


በም​ድረ በዳ በማ​ኅ​በሩ መካ​ከል የነ​በረ እርሱ ነው፤ በደ​ብረ ሲና ከአ​ነ​ጋ​ገ​ረው መል​አ​ክና፤ ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ጋር ለእኛ ሊሰ​ጠን የሕ​ይ​ወ​ትን ቃል የተ​ቀ​በለ እርሱ ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን ወደ እኔ ሰብ​ስ​ባ​ቸው፤ እነ​ርሱ በም​ድር ላይ በሕ​ይ​ወት በሚ​ኖ​ሩ​በት ዘመን ሁሉ እኔን መፍ​ራት ይማ​ሩና ለል​ጆ​ቻ​ቸ​ውም ያስ​ተ​ምሩ ዘንድ ቃሌን ይስሙ ብሎ​ኛ​ልና በኮ​ሬብ በተ​ሰ​በ​ሰ​ባ​ችሁ ጊዜ በፈ​ጣ​ሪ​ያ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ቆማ​ችሁ ንገ​ራ​ቸው።


እና​ን​ተም ቀር​ባ​ችሁ ከተ​ራ​ራው በታች ቆማ​ችሁ ነበር፤ ተራ​ራ​ውም እስከ ሰማይ ድረስ በእ​ሳት ይነ​ድድ ነበር፤ ጨለ​ማና አውሎ ነፋስ፥ ድቅ​ድቅ ጨለ​ማም ነበረ።


እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እነ​ግ​ራ​ችሁ ዘንድ በዚ​ያን ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ቆሜ ነበር፤ እና​ንተ ከእ​ሳቱ ፊት ፈር​ታ​ች​ኋ​ልና፥ ወደ ተራ​ራው አል​ወ​ጣ​ች​ሁ​ምና። እር​ሱም አለ፦


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos