ዘሌዋውያን 7:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ርኩስ ነገር የሚነካውን ሥጋ አይብሉት፤ በእሳት ያቃጥሉት እንጂ። ንጹሕ የሆነ ሰው ሁሉ ግን ከሥጋው ይብላ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ርኩስ ከሆነ ነገር ጋራ የተነካካ ሥጋ ይቃጠል እንጂ አይበላ። ሌላውን ሥጋ ግን በሥርዐቱ መሠረት ንጹሕ የሆነ ማንኛውም ሰው ይብላ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሥጋው ማናቸውንም ርኩስ ነገር ከነካ አይበላ፤ በእሳት ይቃጠል። ሌላውን ሥጋ ግን ንጹሕ የሆነ ሰው ሁሉ ከሥጋው ይብላ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጹሕ የሆነውን ሥጋ ማንኛውም የረከሰ ነገር ቢነካው መቃጠል እንጂ መበላት የለበትም፤ “ንጹሕ የሆነ ሰው ይህን ንጹሕ የሆነውን ሥጋ ይብላ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ርኩስ ነገር የሚነካውን ሥጋ አይብሉት፤ በእሳት ይቃጠል። ንጹሕ የሆነ ሰው ሁሉ ግን ከሥጋው ይብላ። |
በሦስተኛው ቀን ከደኅንነት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ፥ አይሠምርም፤ ላቀረበው ሰው የተጠላ ይሆንበታል እንጂ ቍርባን ሆኖ አይቈጠርለትም፤ ከእርሱም የበላ ሰው ኀጢአቱን ይሸከማል።
ኀጢአት ሳለባት፥ ለእግዚአብሔር ከሆነው ከደኅንነት መሥዋዕት ሥጋ የበላች ሰውነት፥ ያች ሰውነት ከሕዝብዋ ተለይታ ትጥፋ።
ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፥ “ለአይሁዳዊ ሰው ሄዶ ከባዕድ ወገን ጋር መቀላቀል እንደማይገባው ታውቃላችሁ፤ ለእኔ ግን ከሰው ማንንም ቢሆን እንዳልጸየፍና ርኩስ ነው እንዳልል እግዚአብሔር አሳየኝ።
በራሱ ርኩስ የሆነ ነገር እንደሌለ በጌታችን በኢየሱስ ሆኜ ዐውቄአለሁ፤ ተረድቼአለሁም፤ ነገር ግን ማናቸውም ነገር ርኩስ እንደሚሆን ለሚያስብ ያ ለእርሱ ርኩስ ነው።
በመብል ምክንያት የእግዚአብሔርን ፍጥረት አናፍርስ፤ ለንጹሓን ሁሉ ንጹሕ ነው፤ ለሰውስ ክፉው ነገር በመጠራጠር መብላት ነው።
ስለዚህም “ከመካከላቸው ተለይታችሁ ውጡ፤ ከእነርሱም ተለዩ፤ ወደ ርኩሳንም አትቅረቡ፥ እኔም እቀበላችኋለሁ።