Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 6:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ሥጋ​ውን የሚ​ነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆ​ናል፤ ማና​ቸ​ውም ልብስ ደም ቢረ​ጭ​በት የተ​ረ​ጨ​በ​ትን በተ​ቀ​ደሰ ስፍራ ያጥ​ቡ​ታል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ሥጋውን የሚነካ ሁሉ የተቀደሰ ይሆናል፤ ደሙ በልብስ ላይ ቢረጭ፣ ያን ልብስ በተቀደሰ ስፍራ ዕጠብ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ሥጋውን የሚነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆናል፤ በልብስ ላይ ደሙ ከቶ ከተረጨ የተረጨበትን በተቀደሰ ስፍራ ታጥበዋለህ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ሰውም ሆነ ማናቸውም ነገር ያን ሥጋ ቢነካ በቅድስናው ኀይል ይቀሠፋል፤ ማናቸውም የልብስ ዐይነት የእንስሳው ደም ቢፈስበት፥ በተቀደሰ ስፍራ ይታጠብ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ሥጋውን የሚነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆናል፤ ማናቸው ልብስ ደም ቢረጭበት የተረጨበትን በተቀደሰ ስፍራ ታጥበዋለህ።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 6:27
11 Referencias Cruzadas  

ሰባት ቀን መሠ​ዊ​ያ​ውን ታነ​ጻ​ዋ​ለህ፤ ትቀ​ድ​ሰ​ው​ማ​ለህ፤ መሠ​ዊ​ያ​ውም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ይሆ​ናል፤ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም የሚ​ነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆ​ናል።


ሁሉ​ንም ትቀ​ድ​ሳ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ቅዱሰ ቅዱ​ሳ​ንም ይሆ​ናሉ፤ የሚ​ነ​ካ​ቸ​ውም ሁሉ ቅዱስ ይሆ​ናል።


ወደ ውጭ​ውም አደ​ባ​ባይ ወደ ሕዝብ በወጡ ጊዜ ያገ​ለ​ገ​ሉ​በ​ትን ልብ​ሳ​ቸ​ውን ያው​ልቁ፤ በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ዕቃ ቤት ውስጥ ያኑ​ሩት፤ ሕዝ​ቡ​ንም በል​ብ​ሳ​ቸው እን​ዳ​ይ​ቀ​ድሱ ሌላ​ውን ልብስ ይል​በሱ።


ከእ​ነ​ር​ሱም በድ​ና​ቸው በም​ንም ላይ ቢወ​ድቅ እርሱ ርኩስ ነው፤ የዕ​ን​ጨት ዕቃ ወይም ልብስ ወይም ቍር​በት ወይም ከረ​ጢት ቢሆን የሚ​ሠ​ራ​በት ዕቃ ሁሉ እር​ሱን በውኃ ውስጥ ይን​ከ​ሩት፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው፤ ከዚ​ያም በኋላ ንጹሕ ይሆ​ናል።


ከካ​ህ​ናት ወገን ወንድ ሁሉ ይበ​ላ​ዋል፤ በዘ​መ​ና​ችሁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ ነው። ከሚ​ቃ​ጠ​ለው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆ​ናል።”


“ርኩስ ነገር የሚ​ነ​ካ​ውን ሥጋ አይ​ብ​ሉት፤ በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉት እንጂ። ንጹሕ የሆነ ሰው ሁሉ ግን ከሥ​ጋው ይብላ።


አንድ ሰው የተቀደሰ ሥጋ በልብሱ ዘርፍ ቢይዝ፥ በዘርፉም እንጀራ ወይም ወጥ፥ ወይም የወይን ጠጅ፥ ወይም ዘይት፥ ወይም ማናቸውም መብል ቢነካ ያ የተነካው በውኑ ይቀደሳልን? ብለህ ካህናቱን ጠይቃቸው፣ ካህናቱም፦ አይሆንም ብለው መለሱ።


የልብሱንም ጫፍ ብቻ ሊዳስሱ ይለምኑት ነበር፤ የዳሰሱትም ሁሉ ዳኑ።


በልብዋ “ልብሱን ብቻ የዳሰስሁ እንደ ሆነ እድናለሁ፤” ትል ነበረችና።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እን​ግ​ዲህ ይህ ተስፋ ያለን ስለ​ሆን ራሳ​ች​ንን እና​ንጻ፤ ሥጋ​ች​ንን አና​ር​ክስ፤ ነፍ​ሳ​ች​ን​ንም አና​ሳ​ድፍ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በመ​ፍ​ራት የም​ን​ቀ​ደ​ስ​በ​ትን እን​ሥራ።


እነሆ፥ ያ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብላ​ችሁ ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ኀዘን ምንም የማ​ታ​ውቁ እስከ መሆን ደር​ሳ​ችሁ፥ ራሳ​ች​ሁን በበጎ ሥራና በን​ጽ​ሕና እስ​ክ​ታ​ጸኑ ድረስ፥ ትጋ​ት​ንና ክር​ክ​ርን፥ ቍጣ​ንና ፍር​ሀ​ትን፥ ናፍ​ቆ​ት​ንና ቅን​ዐ​ትን፥ በቀ​ል​ንም አደ​ረ​ገ​ላ​ችሁ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos