ደግሞም ገጸ ኅብስት፥ ስስ ቂጣም ቢሆን፥ በምጣድም ቢጋገር፥ ቢለወስም ለእህል ቍርባን በሆነው በመልካሙ ዱቄት በመስፈሪያና በልክ ሁሉ ያገለግሉ ዘንድ ሹሞአቸው ነበር።
ዘሌዋውያን 6:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዘይት ጋር በምጣድ ላይ ያደርጉታል፤ ለውሰውም ያገቡታል፤ ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን የሚፈተት መሥዋዕት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሚገባ በዘይት ተለውሶ በምጣድ ላይ ይጋገር፤ ከዚያም የእህሉን ቍርባን ቈራርሰህ ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ይሆን ዘንድ አቅርብ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዘይት ጋር በምጣድ ላይ ይዘጋጃል፤ ደኅና ተደርጎ ከተለወሰ በኋላ ታመጣዋለህ፤ ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን የተጋገረውን የእህል ቁርባን ቈራርሰህ ታቀርበዋለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዘይት ተለውሶና በሚገባ ተቀላቅሎ እንደ እህል መሥዋዕት ከተጋገረ በኋላ መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የእህል መባ ሆኖ ይቅረብ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዘይት ጋር በምጣድ ላይ ይደረጋል፤ ሲለወስ ታገባዋለህ፤ ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን የእህሉን ቍርባን ቈራርሰህ ታቀርበዋለህ። |
ደግሞም ገጸ ኅብስት፥ ስስ ቂጣም ቢሆን፥ በምጣድም ቢጋገር፥ ቢለወስም ለእህል ቍርባን በሆነው በመልካሙ ዱቄት በመስፈሪያና በልክ ሁሉ ያገለግሉ ዘንድ ሹሞአቸው ነበር።
ለምስጋና ቢያቀርበው፥ ከምስጋናው መሥዋዕት ጋር በዘይት የተለወሰ የቂጣ እንጎቻ፥ በዘይትም የተቀባ ስስ ቂጣ፥ በዘይትም የተለወሰ መልካም የስንዴ ዱቄት ያቀርባል።