La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 5:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“ሰው ባለ​ማ​ወቅ ኀጢ​አት ቢሠራ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ አት​ሥሩ ካላ​ቸው ትእ​ዛ​ዛት አን​ዲ​ቱን ቢተ​ላ​ለፍ፥ ቢታ​ወ​ቀው፥ ኀጢ​አት ስለ​ሆ​ነ​ች​በ​ትም ንስሓ ቢገባ፥

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ማንኛውም ሰው ኀጢአት ቢሠራ፣ እግዚአብሔር አታድርጉ ብሎ ከከለከላቸው ትእዛዞች ሳያውቅ አንዱን ተላልፎ ቢገኝ በደለኛ ነው፤ በኀጢአቱም ይጠየቅበታል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ማናቸውም ሰው ኃጢአት ቢሠራ፥ ጌታም፦ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዱን ቢተላለፍ፥ ባያውቅም፥ ያ ሰው በደለኛ ነው፥ ኃጢአቱንም ይሸከማል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“አንድ ሰው ባለማወቅ ከእግዚአብሔር ትእዛዞች አንዲቱን ቢተላለፍ በደለኛ ይሆናል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ማናቸውም ሰው ኃጢአት ቢሠራ፥ እግዚአብሔርም፦ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዲቱን ቢተላለፍ፥ ባያውቅም፥ ያ ሰው በደለኛ ነው፥ ኃጢአቱንም ይሸከማል።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 5:17
11 Referencias Cruzadas  

“የእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ሁሉ ቢስቱ፥ ነገ​ሩም ከማ​ኅ​በሩ ዐይን ቢሸ​ሸግ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አት​ሥሩ ካላ​ቸው ትእ​ዛ​ዛት አን​ዲ​ቱን ቢተ​ላ​ለፉ፤


“መኰ​ን​ንም ኀጢ​አ​ትን ቢሠራ፥ ሳያ​ው​ቅም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላኩ፦ አት​ሥራ ያለ​ውን ትእ​ዛዝ ቢተ​ላ​ለፍ፥ እን​ዲ​ህም ቢበ​ድል፥


“ከሀ​ገ​ሩም ሕዝብ አንድ ሰው ኀጢ​አ​ትን ሳያ​ውቅ ቢሠራ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ አት​ሥራ ያለ​ውን ትእ​ዛዝ ቢተ​ላ​ለፍ፥ ቢበ​ድ​ልም፥


“ሰው ቢዘ​ነጋ፥ ሳያ​ው​ቅም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​ቀ​ደ​ሰው በማ​ና​ቸ​ውም ነገር ኀጢ​አ​ትን ቢሠራ፥ ለበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከመ​ን​ጋዉ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን በብር ሰቅል የተ​ገ​መ​ተ​ውን አውራ በግ ለበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል።


ነውር የሌ​ለ​በ​ትን በሰ​ቅል የተ​ገ​መ​ተ​ውን አውራ በግ ከመ​ን​ጋው ለበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ወደ ካህኑ ያመ​ጣ​ዋል፤ ካህ​ኑም ሳያ​ውቅ ስለ ሳተው ስሕ​ተት ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይቅር ይባ​ል​ለ​ታል።


እርሱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ንስሓ ገብ​ቶ​አ​ልና።”


ያላ​ወቀ ግን ባይ​ሠ​ራም ቅጣቱ ጥቂት ነው፤ ብዙ ከሰ​ጡት ብዙ ይፈ​ል​ጉ​በ​ታ​ልና። ጥቂት ከሰ​ጡ​ትም ጥቂት ይፈ​ል​ጉ​በ​ታ​ልና።


የሚ​ጠ​ራ​ጠር ግን ቢበላ ይፈ​ረ​ድ​በ​ታል፤ በማ​መን አል​ሆ​ነ​ምና፤ ያለ እም​ነ​ትም የሚ​ደ​ረግ ሁሉ ኀጢ​አ​ትና በደል ነው።