La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 4:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የማ​ኅ​በ​ሩም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች እጆ​ቻ​ቸ​ውን በወ​ይ​ፈኑ ራስ ላይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይጭ​ናሉ፤ ወይ​ፈ​ኑ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያር​ዱ​ታል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የሕዝቡም ሽማግሌዎች በእግዚአብሔር ፊት እጆቻቸውን በወይፈኑ ራስ ላይ ይጫኑ፤ ወይፈኑም በእግዚአብሔር ፊት ይታረድ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የጉባኤውም ሽማግሌዎች እጆቻቸውን በወይፈኑ ራስ ላይ በጌታ ፊት ይጭናሉ፤ ወይፈኑም በጌታ ፊት ይታረዳል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የማኀበሩም አለቆች እጆቻቸውን በኰርማው ራስ ላይ ይጫኑበትና በዚያው በእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ይታረድ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የጉባኤውም ሽማግሌዎች እጆቻቸውን በወይፈኑ ራስ ላይ በእግዚአብሔር ፊት ይጭናሉ፤ ወይፈኑም በእግዚአብሔር ፊት ይታረዳል።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 4:15
16 Referencias Cruzadas  

የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ኑ​ት​ንም አውራ ፍየ​ሎች በን​ጉ​ሡና በጉ​ባ​ኤው ፊት አቀ​ረቡ፤ እጃ​ቸ​ው​ንም ጫኑ​ባ​ቸው፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “አንተ፥ አሮ​ንም፥ ናዳ​ብም፥ አብ​ዩ​ድም፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰባ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ውጡ፤ በሩ​ቁም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስገዱ፤


ሙሴም፥ አሮ​ንም፥ ናዳ​ብም፥ አብ​ዩ​ድም፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰባ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ወጡ፤


“መባ​ውም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ከላ​ሞች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ተባ​ቱን ያቀ​ር​ባል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተቀ​ባ​ይ​ነት እን​ዲ​ኖ​ረው በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ፊት ያቀ​ር​በ​ዋል።


ተቀ​ባ​ይ​ነት ይኖ​ረው ዘንድ ስለ እር​ሱም ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለት ዘንድ እጁን በሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ራስ ላይ ይጭ​ናል።


አሮ​ንም ሁለ​ቱን እጆ​ቹን በደ​ኅ​ነ​ኛው ፍየል ራስ ላይ ይጭ​ናል፤ በላ​ዩም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በደል ሁሉ፥ መተ​ላ​ለ​ፋ​ቸ​ውን ሁሉ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል፤ በፍ​የ​ሉም ራስ ላይ ያሸ​ክ​መ​ዋል፤ በተ​ዘ​ጋ​ጀው ሰውም እጅ ወደ ምድረ በዳ ይሰ​ድ​ደ​ዋል።


የተ​ቀ​ባ​ውም ካህን ከወ​ይ​ፈኑ ደም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ያመ​ጣል፤


ወይ​ፈ​ኑ​ንም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያመ​ጣ​ዋል፤ እጁ​ንም በወ​ይ​ፈኑ ራስ ላይ ይጭ​ነ​ዋል፤ ወይ​ፈ​ኑ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያር​ደ​ዋል።


የኀ​ጢ​አ​ት​ንም መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈን አቀ​ረበ፤ አሮ​ንና ልጆ​ቹም በኀ​ጢ​አቱ መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈን ራስ ላይ እጆ​ቻ​ቸ​ውን ጫኑ።


ሙሴም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆን አውራ በግ አቀ​ረበ፤ አሮ​ንና ልጆ​ቹም በአ​ው​ራው በግ ራስ ላይ እጆ​ቻ​ቸ​ውን ጫኑ።


ሙሴም ለቅ​ድ​ስና የሚ​ሆ​ነ​ውን ሁለ​ተ​ኛ​ውን አውራ በግ አቀ​ረበ፤ አሮ​ንና ልጆ​ቹም በአ​ው​ራው በግ ራስ ላይ እጆ​ቻ​ቸ​ውን ጫኑ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ ለሕ​ዝቡ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ጸሐ​ፍት ይሆኑ ዘንድ የም​ታ​ው​ቃ​ቸ​ውን፥ ሰባ ሰዎች ሰብ​ስ​ብ​ልኝ፤ ወደ ምስ​ክ​ሩም ድን​ኳን አም​ጣ​ቸው፤ በዚ​ያም ከአ​ንተ ጋር አቁ​ማ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በደ​መ​ናው ወረደ፤ ተና​ገ​ረ​ውም፤ በእ​ር​ሱም ላይ ከነ​በ​ረው መን​ፈስ ወስዶ በሰ​ባው ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ላይ አደ​ረገ፤ መን​ፈ​ሱም በላ​ያ​ቸው ባደረ ጊዜ ትን​ቢት ተና​ገሩ፤ ከዚያ በኋላ ግን አል​ተ​ጨ​መ​ረ​ላ​ቸ​ውም።


ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቅ​ር​ባ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በሌ​ዋ​ው​ያን ላይ እጃ​ቸ​ውን ይጫ​ኑ​ባ​ቸው።


ሌዋ​ው​ያ​ኑም በወ​ይ​ፈ​ኖቹ ራሶች ላይ እጆ​ቻ​ቸ​ውን ይጫኑ፤ ለሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ስለ ማስ​ተ​ስ​ረያ አን​ዱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅ​ርብ።