ዘሌዋውያን 4:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወይፈኑን ቍርበት፥ ሥጋውንም ሁሉ፥ ራሱንም፥ እግሮቹንም፥ ሆድ ዕቃውንም፥ ፈርሱንም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን የወይፈኑን ቈዳና ሥጋውን ሁሉ፣ ጭንቅላቱንና እግሮቹን፣ ሆድ ዕቃውንና ፈርሱን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወይፈኑን ቆዳ፥ ሥጋውንም ሁሉ፥ ራሱንም፥ እግሮቹንም፥ ሆድ ዕቃውንም፥ ፈርሱንም፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ቆዳውን፥ ሥጋውን ሁሉ፥ ራሱንና እግሮቹን፥ አንጀቱንና የሆድ ዕቃውን በሙሉ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወይፈኑን ቁርበት፥ ሥጋውንም ሁሉ፥ ራሱንም፥ እግሮቹንም፥ ሆድ ዕቃውንም፥ |
ለማስተስረያም እንዲሆን ደማቸው ወደ መቅደስ የገባውን የኀጢአቱን መሥዋዕት ወይፈንና የኀጢአቱን መሥዋዕት ፍየል ከሰፈሩ ወደ ውጭ ያወጡአቸዋል፤ ቍርበታቸውንም፥ ሥጋቸውንም፥ ፈርሳቸውንም በእሳት ያቃጥላሉ።
ለደኅንነት መሥዋዕት ከታረደው ወይፈን እንደ ተወሰደው ይወስዳል፤ ካህኑም ለሚቃጠል መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ ያቀርበዋል።
ወይፈኑንም ሁሉ ከሰፈሩ ወደ ውጭ ይወስዱታል፤ የፊተኛውንም ወይፈን እንዳቃጠሉ ያቃጥሉታል፤ የማኅበሩ የኀጢአት መሥዋዕት ነውና።
ነገር ግን በመቅደሱ ውስጥ ለማስተስረያ ይሆን ዘንድ ከደሙ ወደ ምስክሩ ድንኳን የሚገባው የኀጢአት መሥዋዕት ሁሉ አይበላም፤ በእሳት ይቃጠላል።