ከእኔ አስቀድመው የነበሩት አለቆች ግን በሕዝቡ ላይ አክብደው ነበር፤ ስለ እንጀራውና ስለ ወይኑ አርባ ሰቅል ብር ይወስዱ ነበር፤ ሎሌዎቻቸውም ደግሞ በሕዝቡ ላይ ይሰለጥኑ ነበር። እኔ ግን እግዚአብሔርን ስለ ፈራሁ እንዲህ አላደረግሁም።
ዘሌዋውያን 25:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድምህ ከአንተ ጋር ይኖር ዘንድ ከእርሱ ምንም ወለድ ወይም ትርፍ አትውሰድ፤ ነገር ግን አምላክህን ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወገንህ በመካከልህ ይኖር ዘንድ ምንም ዐይነት ወለድ አትቀበለው፤ አምላክህን ፍራው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድምህ ከአንተ ጋር እንዲኖር ከእርሱ ምንም ወለድ ወይም ትርፍ አትውሰድ፤ ነገር ግን አምላክህን ፍራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወለድ እንዲከፍል አታድርገው፤ እግዚአብሔርን በመፍራት እስራኤላዊ ወገንህ በአጠገብህ እንዲኖር ፍቀድለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድምህ ከአንተ ጋር ይኖር ዘንድ ከእርሱ ምንም ወለድ ወይም ትርፍ አትውሰድ፤ ነገር ግን አምላክህን ፍራ። |
ከእኔ አስቀድመው የነበሩት አለቆች ግን በሕዝቡ ላይ አክብደው ነበር፤ ስለ እንጀራውና ስለ ወይኑ አርባ ሰቅል ብር ይወስዱ ነበር፤ ሎሌዎቻቸውም ደግሞ በሕዝቡ ላይ ይሰለጥኑ ነበር። እኔ ግን እግዚአብሔርን ስለ ፈራሁ እንዲህ አላደረግሁም።
ቍጣዬም ይጸናባችኋል፤ በሰይፍም አስገድላችኋለሁ፤ ሚስቶቻችሁም መበለቶች፥ ልጆቻችሁም ድሀ-አደጎች ይሆናሉ።
ሕዝቡ እንደ ካህኑ፥ ባሪያውም እንደ ጌታው ባሪያይቱም እንደ እመቤቷ፥ የሚሸጠውም እንደሚገዛው፥ ተበዳሪውም እንደ አበዳሪው፥ ዕዳ ከፋዩም እንደ ዕዳ አስከፋዩ ይሆናል።
እናቴ ሆይ! ለምድር ሁሉ የክርክርና የጥል ሰው የሆንሁትን እኔን ወልደሽኛልና ወዮልኝ! ለማንም አልጠቀምሁም፤ ማንም እኔን አልጠቀመኝም፤ ከሚረግሙኝም የተነሣ ኀይሌ አለቀ።
በአራጣ ቢያበድር፥ አትርፎም ቢወስድ፥ እንደዚህ ያለ ሰው በሕይወት አይኖርም፤ ይህን ርኵሰት ሁሉ አድርጎአልና ፈጽሞ ይሞታል፤ ደሙም በላዩ ይሆናል።
እጁንም ከዐመፅ ቢመልስ፥ አራጣንም አትርፎ ባይወስድ፥ ፍርዴንም ቢያደርግ፥ በትእዛዜም ቢሄድ፥ እርሱ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል እንጂ በአባቱ ኀጢአት አይሞትም።
በአራጣ ባያበድር፥ አትርፎም ባይወስድ፥ እጁንም ከኀጢአት ቢመልስ፥ በሰውና በሰው መካከልም የእውነትን ፍርድ ቢፈርድ፥
በአንቺ ውስጥ ደምን ያፈስሱ ዘንድ መማለጃን ተቀበሉ፤ በአንቺም አራጣና ትርፍ ወስደዋል፤ ቀማኛነትሽንና ኀጢአትሽን ፈጸምሽ፤ እኔንም ረሳሽኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና ሰው ባልንጀራውን አያስጨንቅ፤ ነገር ግን አምላክህን እግዚአብሔርን ፍራ።