የምድርንም አሕዛብ ሸቀጥና ልዩ ልዩ እህል ሊገበዩ በሰንበት ቀን ቢያመጡ በሰንበት ወይም በተቀደሰው ቀን ከእነርሱ አንገዛም፤ ሰባተኛውንም ዓመት እናከብራለን፤ ከሰውም ዕዳ ማስከፈልን እንተዋለን።
ዘሌዋውያን 25:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን በሲና ተራራ ላይ እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሙሴን በሲና ተራራ ላይ እንዲህ አለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን በሲና ተራራ ላይ እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን በሲና ተራራ ላይ እንዲህ አለው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን በሲና ተራራ ላይ እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ |
የምድርንም አሕዛብ ሸቀጥና ልዩ ልዩ እህል ሊገበዩ በሰንበት ቀን ቢያመጡ በሰንበት ወይም በተቀደሰው ቀን ከእነርሱ አንገዛም፤ ሰባተኛውንም ዓመት እናከብራለን፤ ከሰውም ዕዳ ማስከፈልን እንተዋለን።
ሙሴም ለእስራኤል ልጆች ተናገራቸው፤ ተሳዳቢውንም ከሰፈር ወደ ውጭ አወጡት፤ በድንጋይም ወገሩት። የእስራኤልም ልጆች እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ።
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ እኔ ወደምሰጣችሁ ምድር በገባችሁ ጊዜ እኔ የምሰጣችሁ ምድር ታርፋለች፤ ለእግዚአብሔርም ሰንበት ታደርጋለች።
እግዚአብሔርም ሙሴን በሲና ምድረ በዳ በምስክሩ ድንኳን ውስጥ፥ በሁለተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን፥ ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው ዓመት እንዲህ ብሎ ተናገረው፦