ዘሌዋውያን 24:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውም ባልንጀራውን ቢጎዳ፥ እርሱ እንዳደረገ እንዲሁ ይደረግበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማንኛውም ሰው በባልንጀራው ላይ ጕዳት ቢያደርስ፣ የዚያው ዐይነት ጕዳት ይፈጸምበት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውም ባልንጀራው ላይ ጉዳት ቢያደርስ፥ እርሱ እንዳደረገ እንዲሁ ይደረግበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ማንም ሰው በሌላ ሰው ላይ ጒዳት ቢያደርስ የዚያኑ ዐይነት ጒዳት ይድረስበት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውም ባልንጀራውን ቢጐዳ፥ እርሱ እንዳደረገ እንዲሁ ይደረግበት። |
አዶኒቤዜቅም፥ “የእጆቻቸውና የእግሮቻቸው አውራ ጣቶች የተቈረጡ ሰባ ነገሥታት ከገበታዬ በታች ፍርፋሪ ይለቅሙ ነበሩ፤ እኔ እንዳደረግሁ እግዚአብሔር እንዲሁ መለሰልኝ” አለ። ወደ ኢየሩሳሌምም ወሰዱት፥ በዚያም ሞተ።