La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 22:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የተ​ቀ​ጠ​ቀ​ጠ​ውን፥ ወይም የተ​ሰ​በ​ረ​ውን፥ ወይም የተ​ቈ​ረ​ጠ​ውን ወይም የተ​ሰ​ነ​ጋ​ውን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አታ​ቅ​ርቡ፤ በም​ድ​ራ​ች​ሁም እነ​ዚ​ህን አት​ሠዉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አባለዘሩ የተቀጠቀጠ ወይም የተኰላሸ፣ የተሰነጠቀ ወይም የተቈረጠ ማንኛውንም እንስሳ ለእግዚአብሔር አታቅርቡ፤ እነዚህንም በምድራችሁ አትሠዉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የብልቱ ፍሬ የተሰነጋውን ወይም የተቀጠቀጠውን ወይም የተሰበረውን ወይም የተቈረጠውን ለጌታ አታቅርቡ፤ በምድራችሁም እነዚህን አትሠዉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ብልቱ የተበላሸ እንስሳ ለእግዚአብሔር በምድርህ መሥዋዕት አድርገህ አታቅርብ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የተሰነጋውን ወይም የተቀጠቀጠውን ወይም የተሰበረውን ወይም የተቈረጠውን ለእግዚአብሔር አታቅርቡ፤ በምድራችሁም እነዚህን አትሠዉ።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 22:24
4 Referencias Cruzadas  

ወይም ጎባጣ፥ ወይም ድንክ፥ ወይም ዐይነ መጭ​ማጫ፥ ወይም ቅን​ድበ መላጣ፥ ወይም እከ​ካም፥ ወይም ቋቍ​ቻም፥ ወይም የአ​ባ​ለ​ዘሩ ፍሬ አንድ የሆነ ነው​ረኛ ሁሉ አይ​ቅ​ረብ።


ነገር ግን አይ​ሠ​ም​ር​ላ​ች​ሁ​ምና ነውር ያለ​በ​ትን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አታ​ቅ​ርቡ።


በሬው፥ ወይም በጉ ጆሮው፥ ወይም ጅራቱ የተ​ቈ​ረጠ ቢሆን፥ ቈጥ​ረህ የራ​ስህ ገን​ዘብ አድ​ር​ገው እንጂ ለስ​እ​ለት አይ​ቀ​በ​ል​ህም።


“ፍሬ ዘሩ የተ​ቀ​ጠ​ቀጠ፥ አባለ ዘሩም የተ​ቈ​ረጠ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ግባ።