ዘሌዋውያን 20:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውም ከቅርብ ዘመዱ ሚስት ጋር ቢተኛ የቅርብ ዘመዱን ኀፍረተ ሥጋ ገልጦአል፤ ያለ ልጅ ይሞታሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ማንኛውም ሰው ከአጎቱ ሚስት ጋራ ግብረ ሥጋ ቢፈጽም፣ አጎቱን አዋርዷልና ሁለቱም ይጠየቁበታል፤ ያለ ልጅም ይሞታሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውም ከአጎቱ ሚስት ጋር ቢተኛ፥ የአጎቱን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአል፤ ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ፤ ያለ ልጅ ይሞታሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ሰው ከአጐቱ ሚስት ጋር ቢተኛ አጐቱን ያዋረደ ስለ ሆነ እርሱም ሆነ ሴትዮዋ ፍዳቸውን ይቀበላሉ፤ ያለ ልጅም ይቀራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውም ከአጎቱ ሚስት ጋር ቢተኛ፥ የአጎቱን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአል፤ ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ፤ ያለ ልጅ ይሞታሉ። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በዘመኑ አይከናወንምና፥ ከዘሩም በዳዊት ዙፋን የሚቀመጥ አይነሣምና፥ እንግዲህ ወዲህም ለይሁዳ ገዢ አይሾምምና ይህን ሰው እንደ ሞተ ቍጠሪው” አለ።