ዘሌዋውያን 20:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማናቸውም ሰው ከባለ ግዳጅ ሴት ጋር ቢተኛ ኀፍረተ ሥጋዋንም ቢገልጥ፥ ፈሳሽዋን ገልጦአልና፥ እርስዋም የደምዋን ፈሳሽ ገልጣለችና ሁለቱ ከሕዝባቸው መካከል ተለይተው ይጥፉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ማንኛውም ሰው በወር አበባዋ ጊዜ ከሴት ጋራ ግብረ ሥጋ ቢፈጽም፣ የፈሳሿን ምንጭ ገልጧልና፣ እርሷም የፈሳሿን ምንጭ ገልጣለችና ሁለቱም ከሕዝባቸው መካከል ተለይተው ይጥፉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማናቸውም ሰው የወር አበባ ካለባት ሴት ጋር ቢተኛ ኃፍረተ ሥጋዋንም ቢገልጥ፥ ፈሳሽዋን ገልጦአልና፥ እርሷም የደምዋን ፈሳሽ ገልጣለችና ሁለቱ ከሕዝባቸው መካከል ተለይተው ይጥፉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ሰው የወር አበባ ካለባት ሴት ጋር ፍትወታዊ ግንኙነት ቢያደርግ የወር አበባዋን ኀፍረት ገልጠዋል ሁለቱም ከሕዝቡ ተለይተው ይባረሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማናቸውም ሰው ከባለ መርገም ሴት ጋር ቢተኛ ኃፍረተ ሥጋዋንም ቢገልጥ፥ ፈሳሽዋን ገልጦአልና፥ እርስዋም የደምዋን ፈሳሽ ገልጣለችና ሁለቱ ከሕዝባቸው መካከል ተለይተው ይጥፉ። |
በተራራም ላይ ባይበላ፥ ዐይኖቹንም ወደ እስራኤል ቤት ጣዖታት ባያነሣ፥ የባልንጀራውንም ሚስት ባያረክስ፥ አደፍም ወዳለባት ሴት ባይቀርብ፤