Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘሌዋውያን 18:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 “እር​ስ​ዋም በግ​ዳ​ጅዋ ርኵ​ሰት ሳለች ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋን ትገ​ልጥ ዘንድ ሳት​ነጻ በግ​ዳ​ጅዋ ወደ አለች ሴት አት​ቅ​ረብ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 “ ‘በወር አበባዋ ርኩሰት ጊዜ ግብረ ሥጋ ለመፈጸም ወደ ሴት አትቅረብ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 “እርሷም ርኩስ በሆነችበት የወር አበባዋ ጊዜያት ላይ ሳለች ኃፍረተ ሥጋዋን ለመግለጥ ወደ ሴት አትቅረብ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 “በወር አበባዋ ምክንያት ካልነጻች ሴት ጋር ፍትወታዊ ግንኙነት አታድርግ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እርስዋም በመርገምዋ ርኵሰት ሳለች ኃፍረተ ሥጋዋን ትገልጥ ዘንድ ወደ ሴት አትቅረብ።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 18:19
8 Referencias Cruzadas  

ማና​ቸ​ውም ሰው ከባለ ግዳጅ ሴት ጋር ቢተኛ ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋ​ንም ቢገ​ልጥ፥ ፈሳ​ሽ​ዋን ገል​ጦ​አ​ልና፥ እር​ስ​ዋም የደ​ም​ዋን ፈሳሽ ገል​ጣ​ለ​ችና ሁለቱ ከሕ​ዝ​ባ​ቸው መካ​ከል ተለ​ይ​ተው ይጥፉ።


ማንም ከእ​ር​ስዋ ጋር ቢተኛ፥ ግዳ​ጅ​ዋም ቢነ​ካው፥ ሰባት ቀን ርኩስ ነው፤ የሚ​ተ​ኛ​በ​ትም መኝታ ሁሉ ርኩስ ነው።


በአ​ንቺ ውስጥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ኀፍ​ረተ ሥጋ ገለጡ፤ በአ​ን​ቺም ውስጥ አደፍ ያለ​ባ​ትን አዋ​ረዱ።


በተ​ራ​ራም ላይ ባይ​በላ፥ ዐይ​ኖ​ቹ​ንም ወደ እስ​ራ​ኤል ቤት ጣዖ​ታት ባያ​ነሣ፥ የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ው​ንም ሚስት ባያ​ረ​ክስ፥ አደ​ፍም ወዳ​ለ​ባት ሴት ባይ​ቀ​ርብ፤


“ሴት ፈሳሽ ነገር ቢኖ​ር​ባት፥ በሥ​ጋ​ዋም ያለው ፈሳሽ ነገር ደም ቢሆን፥ በግ​ዳ​ጅዋ ሰባት ቀን ትቀ​መ​ጣ​ለች፤ የሚ​ነ​ካ​ትም ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ነው።


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ ሴት ብታ​ረ​ግዝ ወንድ ልጅም ብት​ወ​ልድ፥ ሰባት ቀን ያህል የረ​ከ​ሰች ናት፤


በእ​ኅቷ ላይ እን​ዳ​ት​ቀና ሚስ​ትህ በሕ​ይ​ወት ሳለች የእ​ኅ​ቷን ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ።


ዳዊ​ትም መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ልኮ አስ​መ​ጣት፤ ወደ እር​ሱም ገባች፤ ከር​ኵ​ሰ​ቷም ነጽታ ነበ​ርና ከእ​ር​ስዋ ጋር ተኛ፤ ወደ ቤቷም ተመ​ለ​ሰች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios