ዘሌዋውያን 20:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ማናቸውም ሰው የአባቱን ልጅ ወይም የእናቱን ልጅ እኅቱን ቢያገባ፥ ኀፍረተ ሥጋዋንም ቢያይ፥ እርስዋም ኀፍረተ ሥጋውን ብታይ፥ ይህ ጸያፍ ነገር ነው፤ በሕዝባቸውም ልጆች ፊት ይገደሉ፤ የእኅቱን ኀፍረተ ሥጋ ገልጦአልና ኀጢአቱን ይሸከማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘አንድ ሰው የአባቱ ወይም የእናቱ ልጅ የሆነችውን እኅቱን አግብቶ ግብረ ሥጋ ቢፈጽም፣ አድራጎቱ አሳፋሪ ነው፤ በሕዝባቸው ፊት ከሕዝባቸው ተለይተው ይጥፉ። ሰውየው እኅቱን አዋርዷልና ይጠየቅበታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ማናቸውም ሰው የአባቱን ልጅ ወይም የእናቱን ልጅ እኅቱን ቢያገባ፥ ኃፍረተ ሥጋዋንም ቢያይ፥ ኃፍረተ ሥጋውንም ብታይ፥ ይህ አሳፋሪ ነገር ነው፤ ከሕዝባቸውም ልጆች ፊት ተለይተው ይጥፉ፤ የእኅቱን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአልና በደሉን ይሸከማል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ሰው እኅቱን ወይም በአንድ በኩል ብቻ ከአባቱ ወይም ከእናቱ የተወለደችውን እኅቱን አግብቶ ፍትወታዊ ግንኙነት ቢያደርጉ ይህ አስነዋሪ ነገር በመሆኑ ከሕዝባቸው መካከል ተለይተው ይጥፉ፤ ከእኅቱ ጋር ፍትወታዊ ግንኙነት ስላደረገ ፍዳውን ይቀበላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማናቸውም ሰው የአባቱን ልጅ ወይም የእናቱን ልጅ እኅቱን ቢያገባ፥ ኃፍረተ ሥጋዋንም ቢያይ፥ ኃፍረተ ሥጋውንም ብታይ፥ ይህ ጸያፍ ነገር ነው፤ በሕዝባቸውም ልጆች ፊት ይገደሉ፤ የእኅቱን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአልና ኃጢአቱን ይሸከማል። |
እርስዋም አለችው፥ “ወንድሜ ሆይ፥ አታዋርደኝ፤ እንዲህ ያለ ነገር በእስራኤል ዘንድ አይገባምና ይህን ነውረኛ ሥራ አታድርግ።
ሰውም ከባልንጀራው ሚስት ጋር ሰሰነ፤ አባትም የልጁን ሚስት በኀጢአት አረከሰ፤ በአንቺም ዘንድ ወንድም የአባቱን ልጅ እኅቱን አስነወረ።
የእኅትህን ኀፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የአባትህ ልጅ ወይም የእናትህ ልጅ በቤት ወይም በውጭ የተወለደች ብትሆን፥ ኀፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ።
ማንኛዪቱም ሴት ወደ እንስሳ ብትቀርብ፥ ከእርሱም ጋር ብትገናኝ፥ ሴቲቱንና እንስሳውን ግደሉ፤ ፈጽመው ይገደሉ፤ በደለኞች ናቸው።