ዘሌዋውያን 19:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደንቆሮውን አትስደብ፤ በዕውርም ፊት ዕንቅፋት አታድርግ፤ ነገር ግን አምላክህን እግዚአብሔርን ፍራ፤ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ደንቈሮውን አትርገም፤ በዐይነ ስውሩም ፊት ዕንቅፋት አታኑር፤ ነገር ግን አምላክህን ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መስማት የተሳነውን አትስደብ፥ በዓይነ ስውሩም ፊት ዕንቅፋት አታኑር፥ ነገር ግን አምላክህን ፍራ፤ እኔ ጌታ ነኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደንቆሮውን አትስደብ፤ ዐይነ ዕውሩንም ለማሰናከል በፊቱ እንቅፋት አታኑር፤ አምላክህን ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደንቆሮውን አትስደብ፥ በዕውርም ፊት ዕንቅፋት አታድርግ፥ ነገር ግን አምላክህን ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። |
ከእኔ አስቀድመው የነበሩት አለቆች ግን በሕዝቡ ላይ አክብደው ነበር፤ ስለ እንጀራውና ስለ ወይኑ አርባ ሰቅል ብር ይወስዱ ነበር፤ ሎሌዎቻቸውም ደግሞ በሕዝቡ ላይ ይሰለጥኑ ነበር። እኔ ግን እግዚአብሔርን ስለ ፈራሁ እንዲህ አላደረግሁም።
“በሽበታሙ ፊት ተነሣ፤ ሽማግሌውንም አክብር፤ አምላክህን እግዚአብሔርንም ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና።
እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና ሰው ባልንጀራውን አያስጨንቅ፤ ነገር ግን አምላክህን እግዚአብሔርን ፍራ።
እንግዲህ ከዛሬ ጀምሮ እርስ በርሳችን አንነቃቀፍ፤ ይልቁንም ለወንድም እንቅፋትን ወይም ማሰናከያን ማንም እንዳያኖር ይህን ዐስቡ።
ዳሩ ግን ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ፥ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ።