ዘሌዋውያን 18:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአባትህን ኀፍረተ ሥጋና የእናትህን ኀፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ እናትህ ናትና ኀፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ከእናትህ ጋራ ግብረ ሥጋ በመፈጸም አባትህን አታዋርድ፤ እናትህ ናት፤ ከርሷ ጋራ በግብረ ሥጋ አትገናኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአባትህ ኃፍረተ ሥጋ ነውና የእናትህን ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ እናትህ ናት፤ ኃፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእናትህ ጋር ፍትወታዊ ግንኙነት በማድረግ የአባትህን ክብር አታዋርድ፤ እናትህ ስለ ሆነች የእርስዋን ኀፍረተ ሥጋ አትግለጥ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአባትህን ኃፍረተ ሥጋና የእናትህን ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ እናትህ ናት፤ ኃፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ። |
“ከእናንተም ማንም ሰው ኀፍረተ ሥጋውን ይገልጥ ዘንድ ወደ ሥጋ ዘመዱ ሁሉ አይቅረብ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።
ማናቸውም ሰው እናቲቱንና ልጂቱን ቢያገባ ኀጢአት ነው፤ በመካከላቸው ኀጢአት እንዳይሆን እርሱንና እነርሱን በእሳት ያቃጥሉአቸው።