ዘሌዋውያን 18:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወንድምህን ሚስት ኀፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የወንድምህ ኀፍረተ ሥጋ ነውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ከወንድምህ ሚስት ጋራ ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ ይህ ወንድምህን ያዋርዳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወንድምህን ሚስት ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የወንድምህ ኃፍረተ ሥጋ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዋርሳ ስለ ሆነች ከወንድምህ ሚስት ጋር ፍትወታዊ ግንኙነት አታድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወንድምህን ሚስት ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የወንድምህ ኃፍረተ ሥጋ ነው። |
“መምህር ሆይ! ሙሴ “የአንድ ሰው ወንድም ሚስቱን ትቶ ልጅ ሳያስቀር ቢሞት፥ ወንድሙ ሚስቱን አግብቶ ለወንድሙ ዘር ይተካ፤’ ብሎ ጻፈልን።
ዮሐንስም የአራተኛው ክፍል ገዢ ሄሮድስን የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሄሮድያዳን ስለማግባቱና ሄሮድስ ያደርገው ስለነበረው ክፉ ነገር ሁሉ ይገሥጸው ነበር።
“ወንድማማቾች በአንድነት ቢቀመጡ፥ አንዱም ልጅ ሳይኖረው ቢሞት፥ የሞተው ሰው ሚስት ሌላ ሰው ታገባ ዘንድ ወደ ውጭ አትሂድ፤ ነገር ግን የባልዋ ወንድም ወደ እርስዋ ገብቶ እርስዋን ያግባ፤ ከእርስዋም ጋር ይኑር።