እንበረምም የአባቱን ወንድም ልጅ ዮካብድን አገባ፤ አሮንንና ሙሴን፥ እኅታቸውንም ማርያምን ወለደችለት፤ የእንበረምም የሕይወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው።
ዘሌዋውያን 18:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአባትህን እኅት ኀፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የአባትህ ዘመድ ናትና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ከአባትህ እኅት ጋራ ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ እርሷ የአባትህ የሥጋ ዘመድ ናት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአባትህን እኅት ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የአባትህ ዘመድ ናት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አክስትህ ስለ ሆነች ከአባትህ እኅት ጋር ፍትወታዊ ግንኙነት አታድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአባትህን እኅት ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የአባትህ ዘመድ ናት። |
እንበረምም የአባቱን ወንድም ልጅ ዮካብድን አገባ፤ አሮንንና ሙሴን፥ እኅታቸውንም ማርያምን ወለደችለት፤ የእንበረምም የሕይወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው።
ከአባትህ የተወለደችውን የአባትህን ሚስት ልጅ ኀፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ ከአባትህ የተወለደች እኅትህ ናት፤ ኀፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ።
የአባትህን ወይም የእናትህን እኅት ኀፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ ይህን የሚያደርግ የዘመድን ኀፍረተ ሥጋ ገልጦአል፤ ኀጢአታቸውን ይሸከማሉ።