ዘሌዋውያን 14:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያልታረደችውንም ዶሮ፥ ዝግባውንም ዕንጨት፥ ቀዩንም ግምጃ፥ ሂሶጱንም ወስዶ በምንጭ ውኃ ላይ በታረደችው ዶሮ ደም ውስጥ ይነክራቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሕይወት ያለውንም ወፍ ከዝግባው ዕንጨት፣ ደመቅ ካለው ቀይ ድርና ከሂሶጵ ጋራ በምንጩ ውሃ ላይ በታረደው ወፍ ደም ውስጥ ይንከር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሕይወት ያለውን ወፍ፥ የዝግባውንም እንጨት፥ ቀዩንም ግምጃ፥ ሂሶጱንም ወስዶ ይነክራቸዋል፥ በሕይወትም ያለውን ወፍ በምንጭ ውኃ ላይ በታረደው የወፍ ደም ውስጥ ይዘፍቀዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌላውንም ወፍ ወስዶ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ቊራጭ፥ ከቀዩ ከፈይ ክርና ከሂሶጱ ቅጠል ጋር በአንድነት ቀድሞ በታረደው ወፍ ደም ውስጥ ይንከረው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕያውንም ወፍ ዝግባውንም እንጨት ቀዩንም ግምጃ ሂሶጱንም ወስዶ ከሕያው ወፍ ጋር በምንጭ ውኃ ላይ በታረደው ወፍ ደም ውስጥ ይነክራቸዋል። |
እነሆም፥ የለምጹ ደዌ ከለምጻሙ ላይ ቢጠፋ፥ ካህኑ ስለሚነጻው ሰው ሁለት ንጹሓን ዶሮዎች በሕይወታቸው፥ የዝግባም ዕንጨት፥ ቀይ ግምጃም፥ ሂሶጵም ያመጣ ዘንድ ያዝዛል።
ገና ጥቂት ጊዜ አለ፤ እንግዲህ ወዲህም ዓለም አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ እኔ ሕያው ነኝና፤ እናንተም ሕያዋን ትሆናላችሁ።
እና የእግዚአብሔር ጠላቶቹ ስንሆን በልጁ ሞት ይቅር ካለን፥ ከታረቀን በኋላም በልጁ ሕይወት እንዴት የበለጠ ያድነን!
እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የመልኩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በሥልጣኑ ቃል እየደገፈ ኀጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ፥ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ።