ከዚያም ወደ ቤቴል ወጣ፤ በመንገድም ሲወጣ ልጆች ከከተማዪቱ ወጥተው፥ “አንተ ራሰ በራ! ውጣ! አንተ ራሰ በራ! ውጣ” ብለው አፌዙበት።
ዘሌዋውያን 13:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የሰውም ጠጕር ከራሱ ቢመለጥ እርሱ በራ ነው፤ ነገር ግን ንጹሕ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንድ ሰው የራሱ ጠጕር ከዐናቱ ዐልቆ መላጣ ቢሆን ንጹሕ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የሰውም ጠጉር ከራሱ ቢመለጥ እርሱ ቡሀ ነው፤ ነገር ግን ንጹሕ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ሰው ጠጒሩ ከራሱ ላይ ቢመለጥ ራሰ በራ ነው እንጂ ንጹሕ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰውም ጠጕር ከራሱ ቢመለጥ እርሱ ቡሀ ነው፤ ነገር ግን ንጹሕ ነው። |
ከዚያም ወደ ቤቴል ወጣ፤ በመንገድም ሲወጣ ልጆች ከከተማዪቱ ወጥተው፥ “አንተ ራሰ በራ! ውጣ! አንተ ራሰ በራ! ውጣ” ብለው አፌዙበት።
ለራሳችሁ እዘኑ፤ ጣዖታችሁና መሠዊያችሁ ያሉባት ዲቦን ትጠፋለችና፤ ወደዚያም ወጥታችሁ በሞዓብ ናባው አልቅሱ፤ ወዮም በሉ፤ ራስ ሁሉ በራ ይሆናል፤ ክንድም ሁሉ ይቈረጣል።
ዓመት በዓላችሁንም ወደ ልቅሶ፥ ዝማሬያችሁንም ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፤ ማቅንም በወገብ ሁሉ ላይ፥ ቡሃነትንም በራስ ሁሉ ላይ ላይ አመጣለሁ፤ እንደ ወዳጅ ልቅሶ አደርጋችኋለሁ፤ ከእርሱም ጋር ያሉት እንደ መከራ ቀን ይሆናሉ።
ስለ ሰውነታችሁ ድካም በሰው ልማድ እነግራችኋለሁ፤ ዕወቁ፤ ቀድሞ ሰውነታችሁን ለኀጢአትና ለርኵሰት፥ ለዐመፃም እንደ አስገዛችሁ፥ እንዲሁ አሁንም ሰውነታችሁን ለጽድቅና ለቅድስና አስገዙ።