La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 11:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በም​ድር ላይ በሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀሱ ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች ሁሉ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን አታ​ር​ክሱ፤ በእ​ነ​ር​ሱም እን​ዳ​ት​ረ​ክሱ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን አታ​ር​ክ​ሱ​ባ​ቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በእነዚህ ፍጥረታት ሁሉ ራሳችሁን አስጸያፊ አታድርጉ፤ በእነርሱም ራሳችሁን በማጕደፍ አትርከሱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በሚርመሰመሱ ተንቀሳቃሾች ሁሉ የገዛ አካላችሁን አታጸይፉ፤ እንዳትረክሱም የገዛ አካላችሁን በእነርሱ አታርክሱ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከነዚህ ውስጥ ማንኛውንም በመብላት ራሳችሁን አታርክሱ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾች ሁሉ ሰውነታችሁን አታስጸይፉ፤ በእነርሱም እንዳትረክሱ ሰውነታችሁን አታርክሱባቸው።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 11:43
5 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “ውኃ የሕ​ይ​ወት እስ​ት​ን​ፋስ ያላ​ቸ​ውን ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችና በም​ድር ላይ ከሰ​ማይ በታች የሚ​በ​ርሩ አዕ​ዋ​ፍን ታስ​ገኝ፥” እን​ዲ​ሁም ሆነ።


በም​ድር ላይ ሥጋ ያለው የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰው ሁሉ ወፉም፥ እን​ስ​ሳ​ውም፥ አራ​ዊ​ቱም፥ በም​ድር ላይ የሚ​ር​መ​ሰ​መ​ሰው ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሹ​ም​ሁሉ፥ ሰውም ሁሉ ጠፋ።


እን​ግ​ዲህ በን​ጹ​ሕና በር​ኩስ እን​ስሳ መካ​ከል፥ በን​ጹ​ሕና በር​ኩ​ስም ወፍ መካ​ከል ለየ​ሁ​ላ​ችሁ፤ ርኩ​ሳን ናቸው ብዬ በለ​የ​ኋ​ቸው በእ​ን​ስ​ሳና በወፍ፥ በም​ድ​ርም ተን​ቀ​ሳ​ቃሽ ሁሉ ነፍ​ሳ​ች​ሁን አታ​ር​ክሱ።


ወይም የሚ​ያ​ረ​ክ​ሰ​ውን ተን​ቀ​ሳ​ቃሽ፥ ወይም በሁሉ ዐይ​ነት የረ​ከ​ሰ​ውን ሰው የሚ​ነካ፥