ዘሌዋውያን 11:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም እነዚህን አትበሉም፤ ኩብኩባ የሚመስለውም፥ ፌንጣ የሚመስለውም፥ አሸን የሚመስለውም፥ አንበጣ የሚመስለውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእነዚህ ማንኛውንም ዐይነት አንበጣ፣ ፌንጣና ኵብኵባ መብላት ትችላላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነርሱም እነዚህን ትበላላችሁ፤ አንበጣዎችን በየወገናቸው፥ ደጎብያዎችን በየወገናቸው፥ ፌንጣዎችን በየወገናቸው፥ ኲብኲባዎችን በየወገናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይኸውም አንበጣዎችን፥ በዐይነታቸው ፌንጣዎችን በየዐይነታቸው፥ ኲብኲባዎችን በየዐይነታቸው መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም እነዚህን ትበላላችሁ፤ አራቱን ዓይነት አንበጣዎች በየወገናቸው። |
ነገር ግን ከሚበርሩት፥ አራትም እግሮች ካሉአቸው፥ ከእግሮቻቸውም በላይ በምድር ላይ የሚዘልሉባቸው ጭኖች ካሉአቸው ተንቀሳቃሾች እነዚህን ትበላላችሁ፤