Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕብራውያን 5:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ስለ እር​ሱም የም​ን​ና​ገ​ረው ብዙ ነገር አለን፤ ጆሮ​ዎ​ቻ​ች​ሁም ስለ ፈዘዙ በቃል ልን​ተ​ረ​ጕ​መው ጭንቅ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ስለዚህ ጕዳይ የምንናገረው ብዙ ነገር አለን፤ ነገር ግን ለመማር ዳተኛ ስለ ሆናችሁ ለማስረዳት አስቸጋሪ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ስለ እርሱም የምንናገረው ብዙ ነገር አለን፤ ለማድመጥ በድንዛዜ ላይ ስለ ሆናችሁ፥ ለማስረዳት አስቸጋሪ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ስለዚህ ጉዳይ የምንናገረው ብዙ ነገር አለ፤ ነገር ግን የማስተዋል ችሎታችሁ አነስተኛ ስለ ሆነ ለማስረዳት አስቸጋሪ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ስለ እርሱም የምንናገረው ብዙ ነገር አለን፥ ጆሮቻችሁም ስለ ፈዘዙ በቃል ልንተረጕመው ጭንቅ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 5:11
12 Referencias Cruzadas  

በዐይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአልና ጆሮአቸውም ደንቁሮአል ዐይናቸውንም ጨፍነዋል፤’ የሚል የኢሳይያስ ትንቢት በእነርሱ ይፈጸማል።


በመልእክቱም ሁሉ ደግሞ እንደ ነገረ ስለዚህ ነገር ተናገረ። በእነዚያ ዘንድ ለማስተዋል የሚያስቸግር ነገር አለ፤ ያልተማሩትና የማይጸኑትም ሰዎች ሌሎችን መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህን ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ።


በዐ​ይ​ና​ቸው እን​ዳ​ያዩ፥ በጆ​ሮ​አ​ቸ​ውም እን​ዳ​ይ​ሰሙ፥ በል​ባ​ቸ​ውም እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ውሉ፥ ወደ እኔም እን​ዳ​ይ​መ​ለ​ሱና ይቅር እን​ዳ​ል​ላ​ቸው የዚህ ሕዝብ ልባ​ቸው ደን​ድ​ኖ​አ​ልና፥ ጆሮ​አ​ቸ​ውም ደን​ቁ​ሮ​አ​ልና፥ ዐይ​ና​ቸ​ው​ንም ጨፍ​ነ​ዋ​ልና’።


“የም​ነ​ግ​ራ​ችሁ ብዙ ነገር ነበ​ረኝ፤ ነገር ግን አሁን ልት​ሸ​ከ​ሙት አት​ች​ሉም።


ሲፈ​ት​ነው ይህን አለ እንጂ፥ እር​ሱስ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ያውቅ ነበር።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ ሰነ​ፎች፥ ነቢ​ያ​ትም የተ​ና​ገ​ሩ​ትን ነገር ሁሉ ከማ​መን ልባ​ችሁ የዘ​ገየ፥


“ገና አላስተዋላችሁምን?” አላቸው።


እነ​ዚህ ሕዝ​ቦች በዐ​ይ​ና​ቸው እን​ዳ​ያዩ፥ በጆ​ሮ​አ​ቸ​ውም እን​ዳ​ይ​ሰሙ፥ በል​ባ​ቸ​ውም እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ውሉ ተመ​ል​ሰ​ውም እን​ዳ​ል​ፈ​ው​ሳ​ቸው፥ ልባ​ቸ​ውን አደ​ን​ድ​ነ​ዋ​ልና፥ ጆሮ​አ​ቸ​ው​ንም ደፍ​ነ​ዋ​ልና፥ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም ጨፍ​ነ​ዋ​ልና።


የሳ​ባም ንግ​ሥት የሰ​ሎ​ሞ​ንን ስም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም በሰ​ማች ጊዜ ሰሎ​ሞ​ንን በእ​ን​ቆ​ቅ​ልሽ ትፈ​ት​ነው ዘንድ መጣች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት የዘ​ለ​ዓ​ለም ሊቀ ካህ​ናት አለው።


መም​ህ​ራን ልት​ሆኑ ሲገ​ባ​ችሁ፥ ካመ​ና​ችሁ ጀምሮ በት​ም​ህ​ርት ላይ የቈ​ያ​ችሁ ስለ ሆነ፥ እስከ ዛሬም ገና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃ​ሉን መጀ​መ​ሪያ ትም​ህ​ርት ሊያ​ስ​ተ​ም​ሩ​አ​ችሁ ትወ​ዳ​ላ​ችሁ፤ ወተ​ት​ንም ሊግ​ቱ​አ​ችሁ ትሻ​ላ​ችሁ፤ ጽኑ ምግ​ብ​ንም አይ​ደ​ለም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios