ልጄንም አጠባ ዘንድ በማለዳ ብነሣ፥ ያን የሞተውን ልጅ አገኘሁ፤ ነገር ግን ብርሃን በሆነ ጊዜ ተመለከትሁት፤ እነሆም፥ የወለድሁት ልጄ አልነበረም።”
ሰቈቃወ 4:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጋሜል። አራዊት እንኳ ጡታቸውን ገልጠው ግልገሎቻቸውን አጠቡ፤ የወገኔ ሴት ልጆች ግን እንደ ምድረ በዳ ሰጐን ጨካኞች ሆኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀበሮዎች እንኳን ግልገሎቻቸውን ለማጥባት፣ ጡታቸውን ይሰጣሉ፤ ሕዝቤ ግን በምድረ በዳ እንዳሉ ሰጎኖች፣ ጨካኞች ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጋሜል። ቀበሮች እንኳ ጡቶታቸውን ገልጠው ግልገሎቻቸውን አጠቡ፥ የወገኔ ልጅ ግን እንደ ምድረ በዳ ሰጐን ጨካኝ ሆነች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀበሮዎች እንኳን የወለዱአቸውን ከጡታቸው ይመግባሉ፤ ሕዝቤ ግን እንደ ምድረ በዳ ሰጎኖች ጨካኞች ሆነዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጋሜል። ቀበሮች እንኳ ጡቶታቸውን ገልጠው ግልገሎቻቸውን አጠቡ፥ የወገኔ ልጅ ግን እንደ ምድረ በዳ ሰጐን ጨካኝ ሆነች። |
ልጄንም አጠባ ዘንድ በማለዳ ብነሣ፥ ያን የሞተውን ልጅ አገኘሁ፤ ነገር ግን ብርሃን በሆነ ጊዜ ተመለከትሁት፤ እነሆም፥ የወለድሁት ልጄ አልነበረም።”
ተኵላዎችም በዚያ ያድራሉ፤ ቀበሮዎችም በሚያማምሩ አዳራሾቻቸው ይዋለዳሉ፤ ይህም ሁሉ ፈጥኖ ይሆናል፤ አይዘገይምም።
“በውኑ ሴት፥ ልጅዋን ትረሳለችን? ከማኅፀንዋ ለተወለደውስ አትራራምን? ሴት ይህን ብትረሳ፥ እኔ አንቺን አልረሳሽም።
የወንዶችና የሴቶች ልጆቻቸውንም ሥጋ አበላቸዋለሁ፤ ሁሉም እያንዳንዳቸው ጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውን የሚሹት በሚያስጨንቋቸው ጭንቀትና መከበብ የባልንጀሮቻቸውን ሥጋ ይበላሉ።
ሬስ። አቤቱ፥ እይ፤ ተመልከት ማንን እንዲህ ቃረምህ? በውኑ ሴቶች የማኅፀናቸውን ፍሬ፥ ያሳደጓቸውን ሕፃናት ይበላሉን? በውኑ ካህኑና ነቢዩ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ይገደላሉን?
ስለዚህ በመካከልሽ አባቶች ልጆቻቸውን ይበላሉ፤ ልጆችም አባቶቻቸውን ይበላሉ፤ ፍርድንም አደርግብሻለሁ፤ ከአንቺም የቀረውን ሁሉ ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናለሁ።