ሰቈቃወ 4:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮድ። የርኅሩኆች ሴቶች እጆች ልጆቻቸውን ቀቅለዋል፤ የወገኔ ሴት ልጅ በመቀጥቀጥዋ መብል ሆኖአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቤ ባለቀበት ጊዜ፣ ምግብ እንዲሆኗቸው፣ ርኅሩኆቹ ሴቶች በገዛ እጆቻቸው፣ ልጆቻቸውን ቀቀሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮድ። የርኅሩኆች ሴቶች እጆች ልጆቻችውን ቀቅለዋል፥ የወገኔ ሴት ልጅ በመቀጥቀጥዋ መብል ሆኗቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የርኅሩኅ ሴቶች እጆች የገዛ ልጆቻቸውን ቀቀሉ፤ ከተማዋ በተደመሰሰች ጊዜ እነዚያ የተቀቀሉ ልጆች ለሰዎች ምግብ ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮድ። የርኅሩኆች ሴቶች እጆች ልጆቻችውን ቀቅለዋል፥ የወገኔ ሴት ልጅ በመቀጥቀጥዋ መብል ሆኑአቸው። |
ጩኸትና ፍጅትም የተሞላብሽ ከተማ ሆይ፥ ቍስለኞችሽ በሰይፍ የቈሰሉ አይደሉም፤ በአንቺ ውስጥ የተገደሉትም በሰልፍ የተገደሉ አይደሉም።
“በውኑ ሴት፥ ልጅዋን ትረሳለችን? ከማኅፀንዋ ለተወለደውስ አትራራምን? ሴት ይህን ብትረሳ፥ እኔ አንቺን አልረሳሽም።
የወንዶችና የሴቶች ልጆቻቸውንም ሥጋ አበላቸዋለሁ፤ ሁሉም እያንዳንዳቸው ጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውን የሚሹት በሚያስጨንቋቸው ጭንቀትና መከበብ የባልንጀሮቻቸውን ሥጋ ይበላሉ።
ካፍ። ሕፃኑና ጡት የሚጠባው በከተማዪቱ ጎዳና ላይ ሲዝሉ፥ ዐይኔ በእንባ ደከመች፤ ልቤም ታወከ፤ ስለ ወገኔ ሴት ልጅ መከራ ክብሬ በምድር ላይ ተዋረደ።
ሬስ። አቤቱ፥ እይ፤ ተመልከት ማንን እንዲህ ቃረምህ? በውኑ ሴቶች የማኅፀናቸውን ፍሬ፥ ያሳደጓቸውን ሕፃናት ይበላሉን? በውኑ ካህኑና ነቢዩ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ይገደላሉን?
ጋሜል። አራዊት እንኳ ጡታቸውን ገልጠው ግልገሎቻቸውን አጠቡ፤ የወገኔ ሴት ልጆች ግን እንደ ምድረ በዳ ሰጐን ጨካኞች ሆኑ።
ስለዚህ በመካከልሽ አባቶች ልጆቻቸውን ይበላሉ፤ ልጆችም አባቶቻቸውን ይበላሉ፤ ፍርድንም አደርግብሻለሁ፤ ከአንቺም የቀረውን ሁሉ ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናለሁ።