ሰቈቃወ 1:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላሜድ። እናንተ መንገድ ዐላፊዎች ሁሉ! በእናንተ ዘንድ ምንም የለምን? እግዚአብሔር በጽኑ ቍጣው ቀን እኔን እንዳስጨነቀበት በእኔ ላይ እንደ ተደረገው እንደ እኔ ቍስል የሚመስል ቍስል እንዳለ ተመልከቱ፤ እዩም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እናንተ መንገድ ዐላፊዎች ሁሉ፤ ይህ ለእናንተ ምንም አይደለምን? ተመልከቱ፤ እዩም፤ በጽኑ ቍጣው ቀን፣ እግዚአብሔር ያመጣብኝን፣ በእኔ ላይ የደረሰውን፣ የእኔን መከራ የመሰለ መከራ አለን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ላሜድ። እናንተ መንገድ አላፊዎች ሁሉ፥ በእናንተ ዘንድ ምንም የለምን? እግዚአብሔር በጽኑ ቁጣው ቀን እኔን እንዳስጨነቀበት በእኔ ላይ እንደተደረገው እንደ እኔ መከራ የሚመስል መከራ እንዳለ ተመልከቱ፥ እዩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ጽኑ ቊጣውን በእኛ ላይ ባወረደበት ቀን በእኛ ላይ እንደ ደረሰው ያለ መከራ የደረሰበት ሰው ያለ እንደ ሆነ እናንተ አላፊ አግዳሚዎች እስቲ እዩ ተመልከቱ! ይህ ሁኔታ ለእናንተ ቀላል ነውን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላሜድ። እናንተ መንገድ አላፊዎች ሁሉ፥ በእናንተ ዘንድ ምንም የለምን? እግዚአብሔር በጽኑ ቍጣው ቀን እኔን እንዳስጨነቀበት በእኔ ላይ እንደ ተደረገው እንደ እኔ መከራ የሚመስል መከራ እንዳለ ተመልከቱ፥ እዩ። |
ስለዚህ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር መዓት በጽኑ ቍጣው ቀንም ሰማያት ይንቀጠቀጣሉ፤ ምድርም ከመሠረቷ ትናወጣለች።
እስራኤል ለአንተ መሳቂያ አልሆነምን? ወይስ በሌቦች መካከል ተገኝቶአልን? ስለ እርሱ በተናገርህ ጊዜ ራስህን ትነቀንቃለህ።
ጻዴ። ቃሉን አማርሬአለሁና እግዚአብሔር ጻድቅ ነው። እናንተ አሕዛብ ሁሉ እባካችሁ ስሙ፤ መከራዬንም ተመልከቱ፤ ደናግሎችና ጐልማሶች ተማርከው ሄደዋልና።
አሌፍ። እግዚአብሔር በቍጣው መቅሠፍት የጽዮንን ሴት ልጅ ምንኛ አጠቈራት! የእስራኤልን ክብር ከሰማይ ወደ ምድር ጣለ፤ በቍጣውም ቀን የእግሩን መረገጫ አላሰበም።
ሜም። የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ምን እመሰክርልሻለሁ? በምንስ እመስልሻለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ማን ያድንሻል? ማንስ ያጽናናሻል? ስብራትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና፤ የሚፈውስሽ ማን ነው?
የጨለማና የነፋስ ቀን፥ የደመናና የጉም ቀን ነው፤ ታላቅና ብርቱ ሕዝብ በተራሮች ላይ እንደ ወገግታ ተዘርግቶአል፤ ከዘለዓለምም ጀምሮ እንደ እርሱ ያለ አልነበረም፤ ከእርሱም በኋላ እስከ ልጅ ልጅ ድረስ እንደ እርሱ ያለ አይሆንም።