ያዕቆብም ከሁለቱ ወንዞች መካከል በተመለሰ ጊዜ በከነዓን ምድር ወዳለችው ወደ ሰቂሞን ከተማ ወደ ሴሎም መጣ፤ በከተማዪቱም ፊት ለፊት ሰፈረ።
መሳፍንት 9:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሩበኣል ልጅ አቤሜሌክም ወደ ሰቂማ ወደ እናቱ ወንድሞች ሄደ፤ ለእነርሱም፥ ለእናቱ አባት ቤተ ሰቦችም ሁሉ እንዲህ ሲል ተናገረ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሩባኣል ልጅ አቢሜሌክ ወደ እናቱ ወንድሞች ወደ ሴኬም ሄደ። እነርሱንና የእናቱን ጐሣዎች በሙሉ እንዲህ አላቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይሩባኣል ልጅ አቤሜሌክ ወደ እናቱ ወንድሞች ወደ ሴኬም ሄደ። እነርሱንና የእናቱን ጐሣዎች በሙሉ እንዲህ አላቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጌዴዎን ልጅ አቤሜሌክ የእናቱ ዘመዶች ወደሚኖሩበት ወደ ሴኬም ከተማ ሄዶ ለእናቱ ወገኖች ሁሉ እንዲህ አላቸው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይሩበኣል ልጅ አቤሜሌክም ወደ ሴኬም ወደ እናቱ ወንድሞች ሄደ፥ ለእነርሱም ለእናቱ አባት ቤተ ሰቦችም ሁሉ፦ |
ያዕቆብም ከሁለቱ ወንዞች መካከል በተመለሰ ጊዜ በከነዓን ምድር ወዳለችው ወደ ሰቂሞን ከተማ ወደ ሴሎም መጣ፤ በከተማዪቱም ፊት ለፊት ሰፈረ።
በንጉሡ ዘንድ ሊፋረዱ ለሚመጡ ለእስራኤል ሁሉ አቤሴሎም እንዲህ ያደርግ ነበር፤ አቤሴሎምም የእስራኤልን ሰዎች ልብ ማረከ።
ከዚህም በኋላ እስራኤል በሙሉ ኢዮርብዓም ከግብፅ እንደ ተመለሰ በሰሙ ጊዜ ልከው ወደ ሸንጎአቸው ጠሩት፤ በእስራኤልም ሁሉ ላይ አነገሡት። ከብቻው ከይሁዳና ከብንያም ነገድ በቀር የዳዊትን ቤት የተከተለ ማንም አልነበረም።
እነርሱም፥ “ሕግ ከካህን፥ ምክርም ከጠቢብ፥ ቃልም ከነቢይ አይጠፋምና ኑ፤ በኤርምያስ ላይ ምክርን እንምከር። ኑ፤ በምላስ እንምታው፤ ቃሉንም ሁሉ አናዳምጥ” አሉ።
ጢማቸውን ላጭተው፥ ልብሳቸውንም ቀድደው እያለቀሱ ወደ እግዚአብሔር ቤት ያቀርቡ ዘንድ የእህል ቍርባንና ዕጣን በእጃቸው የያዙ፥ ሰማንያ ሰዎች ከሴኬምና ከሴሎ፥ ከሰማርያም መጡ።
በንፍታሌም ባለው በተራራማው ሀገር በገሊላ ቃዴስን፥ በኤፍሬምም ባለው በተራራማው ሀገር ሴኬምን፥ በይሁዳም ባለው በተራራማው ሀገር ኬብሮን የምትባለውን የአርቦቅን ከተማ ለዩ።
እርሱም ለእስራኤል በጎ ነገርን ሁሉ እንዳደረገ መጠን፥ እነርሱ ይሩበኣል ለተባለው ለጌዴዎን ቤት ወረታ አላደረጉም።