እነዚያ ይስማኤላውያን ነጋዴዎችም ሲያልፉ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጕድጓድ ጐትተው አወጡት፤ ለይስማኤላውያንም ዮሴፍን በሃያ ብር ሸጡት፤ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወሰዱት።
መሳፍንት 8:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ሰዎች ጌዴዎንን፥ “ከምድያም እጅ አድነኸናልና አንተ፥ ልጅህም፥ የልጅ ልጅህም ደግሞ ግዙን” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያንም ጌዴዎንን፣ “ከምድያማውያን እጅ ታድገኸናልና አንተ፣ ልጅህና የልጅ ልጅህ ግዙን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤላውያንም ጌዴዎንን፥ “ከምድያማውያን እጅ ታድገኸናልና አንተ፥ ልጅህና የልጅ ልጅህ ግዙን” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን ጌዴዎንን “አንተ ከምድያማውያን እጅ አድነኸናልና አንተና ከአንተም በኋላ ልጆችህ እንዲሁም የልጅ ልጆችህ ገዢዎቻችን ሁኑ፤” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ሰዎች ጌዴዎንን፦ ከምድያም እጅ አድነኸናልና አንተ ልጅህም የልጅ ልጅህም ደግሞ ግዙን አሉት። |
እነዚያ ይስማኤላውያን ነጋዴዎችም ሲያልፉ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጕድጓድ ጐትተው አወጡት፤ ለይስማኤላውያንም ዮሴፍን በሃያ ብር ሸጡት፤ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወሰዱት።
ዛብሄልና ስልማናም፥ “ኀይልህ እንደ ጐልማሳ ኀይል ነውና አንተ ተነሥተህ ውደቅብን” አሉት። ጌዴዎንም ተነሥቶ ዛብሄልንና ስልማናን ገደለ፤ በግመሎቻቸውም አንገት የነበሩትን ሥሉሴዎች ማረከ።
የአሞንም ልጆች ንጉሥ ናዖስ እንደ መጣባችሁ ባያችሁ ጊዜ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ንጉሣችሁ ሳለ፦ እንዲህ አይሁን፤ ነገር ግን ንጉሥ አንግሥልን አላችሁኝ።
እንዲህም አሉት፥ “እነሆ፥ አንተ ሸምግለሃል፤ ልጆችህም በመንገድህ አይሄዱም፤ አሁንም እንደ ሌሎች አሕዛብ ሁሉ የሚፈርድልን ንጉሥ አንግሥልን።”