Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 8:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ጌዴ​ዎ​ንም፥ “እኔ አል​ገ​ዛ​ች​ሁም፤ ልጄም አይ​ገ​ዛ​ች​ሁም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይገ​ዛ​ች​ኋል እንጂ” አላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ጌዴዎን ግን መልሶ፣ “እኔም ሆንሁ ልጄ አንገዛችሁም፤ የሚገዛችሁ እግዚአብሔር ነው” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ጌዴዎን ግን መልሶ፥ “እኔም ሆንሁ ልጄ አንገዛችሁም፤ የሚገዛችሁ ጌታ ነው” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ጌዴዎንም “እኔም ሆንኩ ልጄ የእናንተ ገዢዎች አንሆንም፤ የእናንተ ገዢ ራሱ እግዚአብሔር ነው” ሲል መለሰላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ጌዴዎንም፦ እኔ አልገዛችሁም፥ ልጄም አይገዛችሁም፥ እግዚአብሔር ይገዛችኋል አላቸው።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 8:23
14 Referencias Cruzadas  

እስ​ራ​ኤል በፈ​ጣ​ሪው ደስ ይለ​ዋል፥ የጽ​ዮ​ንም ልጆች በን​ጉ​ሣ​ቸው ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋሉ።


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነውና ቸል አይ​ለ​ንም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈራ​ጃ​ችን ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችን ነው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንጉ​ሣ​ችን ነው፤ እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያድ​ነ​ናል።


ከጥ​ንት እን​ዳ​ል​ገ​ዛ​ኸን ስም​ህም በእኛ ላይ እን​ዳ​ል​ተ​ጠራ ሆነ​ና​ልና።


ደስ የሚ​ላ​ች​ሁን እን​ድ​ታ​ደ​ርጉ እን​ረ​ዳ​ች​ኋ​ለን እንጂ እን​ድ​ታ​ምኑ ግድ የም​ን​ላ​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ በእ​ም​ነት ቆማ​ች​ኋ​ልና።


ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኀይል አትግዙ፤


የገ​ለ​ዓድ ሕዝብ አለ​ቆ​ችም እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “ከአ​ሞን ልጆች ጋር መዋ​ጋ​ትን የሚ​ጀ​ምር ማን ነው? እርሱ በገ​ለ​ዓድ ሰዎች ሁሉ ላይ አለቃ ይሆ​ናል” አሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መሳ​ፍ​ን​ትን ባስ​ነ​ሣ​ላ​ቸው ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከመ​ስ​ፍኑ ጋር ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሚ​ዋ​ጉ​አ​ቸው ሰዎች ፊት ከመ​ከ​ራ​ቸው የተ​ነሣ ይቅር ብሏ​ቸ​ዋ​ልና በመ​ስ​ፍኑ ዘመን ሁሉ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ አዳ​ና​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ጌዴ​ዎ​ንን፥ “ከም​ድ​ያም እጅ አድ​ነ​ኸ​ና​ልና አንተ፥ ልጅ​ህም፥ የልጅ ልጅ​ህም ደግሞ ግዙን” አሉት።


ዛሬ ግን ከመ​ከ​ራ​ች​ሁና ከጭ​ን​ቃ​ችሁ ሁሉ ያዳ​ና​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ንቃ​ችሁ፦ ‘እን​ዲህ አይ​ሁን፤ ነገር ግን ንጉሥ አን​ግ​ሥ​ልን’ አላ​ች​ሁት። አሁ​ንም በየ​ነ​ገ​ዳ​ች​ሁና በየ​ወ​ገ​ና​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቁሙ” አላ​ቸው።


የአ​ሞ​ንም ልጆች ንጉሥ ናዖስ እንደ መጣ​ባ​ችሁ ባያ​ችሁ ጊዜ፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንጉ​ሣ​ችሁ ሳለ፦ እን​ዲህ አይ​ሁን፤ ነገር ግን ንጉሥ አን​ግ​ሥ​ልን አላ​ች​ሁኝ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos