ሑሳምም ሞተ፤ በእርሱም ፈንታ የምድያምን ሰዎች በሞዓብ ሜዳ የገደለ የቤዳድ ልጅ አዳድ ነገሠ፤ የከተማዋም ስም ዓዊት ተባለ።
መሳፍንት 7:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ሰዎች ከንፍታሌምና ከአሴር፥ ከምናሴም ሁሉ ተሰብስበው ምድያምን አሳደዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በንፍታሌም፣ በአሴርና በመላው የምናሴ ምድር የሚገኙ እስራኤላውያን ተጠርተው ወጡ፤ ምድያማውያንንም አሳደዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በንፍታሌም፥ በአሴርና በመላው የምናሴ ምድር የሚገኙ እስራኤላውያን ተጠርተው ወጡ፤ ምድያማውያንንም አሳደዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የንፍታሌም፥ የአሴርና መላው የምናሴ ነገድ ተጠርተው ወጥተው ምድያማውያንን አሳደዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ሰዎች ከንፍታሌምና ከአሴር ከምናሴም ሁሉ ተሰብስበው ምድያምን አሳደዱ። |
ሑሳምም ሞተ፤ በእርሱም ፈንታ የምድያምን ሰዎች በሞዓብ ሜዳ የገደለ የቤዳድ ልጅ አዳድ ነገሠ፤ የከተማዋም ስም ዓዊት ተባለ።
አክዓብም ኤልያስን፥ “ጠላቴ ሆይ! አገኘኸኝን?” አለው። እርሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት፥ “አግኝቼሃለሁ፤ ታስቈጣው ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አድርገሃልና እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
እነሆ፥ ክፉ ነገር አመጣብሃለሁ፤ እሳትን ከኋላህ አነድዳለሁ፤ ዐጥር ተጠግቶ እስከሚሸን ድረስ የአክዓብን ዘር አጠፋዋለሁ፤ በእስራኤል ውስጥ ያሉትንም፥ የሌሉትንም እነቅላለሁ፤
ወደ ምናሴም ነገድ ሁሉ መልእክተኞችን ላከ፤ እርሱም ከኋላው ሆኖ ጮኸ፤ መልእክተኞችንም ወደ አሴርና ወደ ዛብሎን ወደ ንፍታሌምም ላከ፤ እነርሱም ሊቀበሉአቸው ወጡ።