Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 6:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 ወደ ምና​ሴም ነገድ ሁሉ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እር​ሱም ከኋ​ላው ሆኖ ጮኸ፤ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ች​ንም ወደ አሴ​ርና ወደ ዛብ​ሎን ወደ ንፍ​ታ​ሌ​ምም ላከ፤ እነ​ር​ሱም ሊቀ​በ​ሉ​አ​ቸው ወጡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 እንዲሁም በመላው የምናሴ ምድር መልእክተኞቹን ልኮ እንዲከተሉት ጥሪ አደረገ፤ ደግሞም የአሴር፣ የዛብሎንና የንፍታሌም ሰዎች ወጥተው እንዲገጥሟቸው መልእክተኛ ላከባቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 እንዲሁም በመላው የምናሴ ምድር መልእክተኞቹን ልኮ እንዲከተሉት ጥሪ አደረገ፤ ደግሞም የአሴር፥ የዛብሎንና የንፍታሌም ሰዎች ወጥተው እንዲገጥሟቸው መልእክተኛ ላከባቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 የምናሴን ነገድ ሁሉ መልእክት ልኮ ይከተሉት ዘንድ አስጠራቸው፤ እንዲሁም ወደ አሴር፥ ወደ ዛብሎንና ወደ ንፍታሌም ነገዶች መልእክተኞች ላከ፤ እነርሱም ከሌሎቹ ጋር ለመሰለፍ ወጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 ወደ ምናሴም ነገድ ሁሉ መልክተኞችን ሰደደ እነርሱም ደግሞ ተጠርተው በኋላው ተከተሉት፥ መልክተኞችንም ወደ አሴርና ወደ ዛብሎን ወደ ንፍታሌምም ሰደደ፥ እነርሱም ሊገናኙአቸው ወጡ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 6:35
6 Referencias Cruzadas  

ባር​ቅም ዛብ​ሎ​ን​ንና ንፍ​ታ​ሌ​ምን ወደ ቃዴስ ጠራ​ቸው፤ ዐሥር ሺህም ሰዎች ተከ​ት​ለ​ውት ወጡ፤ ዲቦ​ራም ከእ​ርሱ ጋር ወጣች።


ዲቦ​ራም ልካ ከቃ​ዴስ ንፍ​ታ​ሌም የአ​ቢኒ​ሔ​ምን ልጅ ባር​ቅን ጠርታ እን​ዲህ አለ​ችው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ያዘ​ዘህ አይ​ደ​ለ​ምን? ሄደህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፤ ከአ​ን​ተም ጋር ከን​ፍ​ታ​ሌ​ምና ከዛ​ብ​ሎን ልጆች ዐሥር ሺህ ሰዎች ውሰድ፤


ዛብ​ሎን ነፍ​ሱን ወደ ሞት ያሳ​ለፈ ሕዝብ ነው፤ ንፍ​ታ​ሌ​ምም በሀ​ገሩ ኮረ​ብታ ላይ ነው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ከን​ፍ​ታ​ሌ​ምና ከአ​ሴር፥ ከም​ና​ሴም ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው ምድ​ያ​ምን አሳ​ደዱ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሁን እን​ግ​ዲህ፥ “የፈራ፥ የደ​ነ​ገ​ጠም ከገ​ለ​ዓድ ተራራ ተነ​ሥቶ ይመ​ለስ ብለህ በሕ​ዝቡ ጆሮ አውጅ” አለው። ከሕ​ዝ​ቡም ሃያ ሁለት ሺህ ተመ​ለሱ፤ ዐሥ​ርም ሺህ ቀሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos