እንስራሽን አዘንብለሽ ውኃ አጠጭኝ የምላት እርስዋም፦ ‘አንተ ጠጣ፥ ግመሎችህን ደግሞ እስኪረኩ አጠጣለሁ’ የምትለኝ ድንግል፥ እርስዋ ለባሪያህ ለይስሐቅ ያዘጋጀሃት ትሁን፤ በዚህም ለጌታዬ ለአብርሃም ምሕረትን እንዳደረግህ አውቃለሁ።”
መሳፍንት 7:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚናገሩትንም አድምጣቸው፤ ከዚያም በኋላ እጆችህ ይበረታሉ፤ ወደ ሰፈርም ትወርዳለህ” አለው። እርሱም ከሎሌው ፋራን ጋር ከሰፈሩ በአንድ ወገን የአምሳ አለቃ ጦር ወደ ሰፈረበት ወረደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚሉትንም ስማ፤ ከዚያ በኋላ በሰፈሩ ላይ አደጋ ለመጣል ድፍረት ታገኛለህ።” ስለዚህም ጌዴዎን አገልጋዩን ፉራን አስከትሎ እስከ ሰፈሩ ዳርቻ ወረደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚሉትንም አድምጥ፤ ከዚያ በኋላ በሰፈሩ ላይ አደጋ ለመጣል ድፍረት ታገኛለህ፤” ስለዚህም ጌዴዎን አገልጋዩን ፉራን አስከትሎ እስከ ሰፈሩ ዳርቻ ወረደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም የሚሉትን ትሰማለህ፤ ከዚያም በኋላ በእነርሱ ላይ አደጋ ለመጣል ድፍረት ታገኛለህ፤”። ስለዚህ ጌዴዎንና አገልጋዩ ፑራ ወደ ጠላት ሰፈር ዳርቻ ወረዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚናገሩትንም ትሰማለህ፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ትወርድ ዘንድ እጅህ ትበረታለች አለው። እርሱና ሎሌው ፉራ በሰፈሩ ዳርቻ ወደ ነበሩት ሰልፈኞች ወረዱ። |
እንስራሽን አዘንብለሽ ውኃ አጠጭኝ የምላት እርስዋም፦ ‘አንተ ጠጣ፥ ግመሎችህን ደግሞ እስኪረኩ አጠጣለሁ’ የምትለኝ ድንግል፥ እርስዋ ለባሪያህ ለይስሐቅ ያዘጋጀሃት ትሁን፤ በዚህም ለጌታዬ ለአብርሃም ምሕረትን እንዳደረግህ አውቃለሁ።”
እግዚአብሔርም ደስ አሰኝቶአቸዋልና፥ የእስራኤልንም አምላክ የእግዚአብሔርን ቤት ለመሥራት እጃቸውን ያጸና ዘንድ የአሦርን ንጉሥ ልብ ወደ እነርሱ መልሶአልና የቂጣውን በዓል ሰባት ቀን በደስታ አደረጉ።
ነገር ግን እግዚአብሔር ሕዝቡን በዙሪያ መንገድ በኤርትራ ባሕር ባለችው ምድረ በዳ መራቸው። የእስራኤልም ልጆች በአምስተኛው ትውልድ ከግብፅ ምድር ወጡ።
የሰፈሩም ሰዎች፦ ዮናታንንና ጋሻ ጃግሬውን “ወደ እኛ ውጡ፤ አንድ ነገርንም እንነግራችኋለን” አሉ። ዮናታንም ጋሻ ጃግሬውን “እግዚአብሔር በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጥቶአቸዋልና ተከተለኝ” አለው።
ዳዊትም ኬጤያዊዉን አቤሜሌክንና የሶርህያን ልጅ የኢዮአብን ወንድም አቢሳን፥ “ወደ ሳኦል ወደ ሰፈሩ ከእኔ ጋር የሚገባ ማን ነው?” ብሎ ጠየቃቸው፤ አቢሳም፥ “እኔ ከአንተ ጋር እገባለሁ” አለ።