እግዚአብሔርም፥ “ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ለአባቶቻችሁም እንዳዘዝሁት፥ በባሪያዎቼ በነቢያት የላክሁላችሁን ትእዛዜንና ሥርዐቴን፥ ሕጌንም ሁሉ ጠብቁ” ብሎ በነቢዩ ሁሉና በባለ ራእዩ አፍ ሁሉ በእስራኤልና በይሁዳ መሰከረ።
መሳፍንት 6:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተንም፦ እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነኝ፤ በምድራቸው የተቀመጣችሁባቸውን የአሞሬዎናውያንን አማልክት አትፍሩ አልኋችሁ። እናንተ ግን ቃሌን አልሰማችሁም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተንም፣ ‘እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፤ በምድራቸው ላይ የምትኖሩባቸው የአሞራውያንን አማልክት አታምልኩ’ አልኋችሁ፤ እናንተ ግን አላዳመጣችሁኝም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተንም፥ “‘እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ፤ በምድራቸው ላይ የምትኖሩባቸው የአሞራውያንን አማልክት አታምልኩ’ አልኋችሁ፤ እናንተ ግን አላዳመጣችሁኝም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩና አሁን ምድራቸውን የወረሳችኋቸውን የአሞራውያንን ባዕዳን አማልክት እንዳታመልኩ ነግሬአችሁ ነበር፤ እናንተ ግን አልሰማችሁኝም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተም፦ እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነኝ፥ በምድራቸው የተቀመጣችሁባቸውን የአሞራያውያንን አማልክት አትፍሩ አልኋችሁ። እናንተ ግን ድምፄን አልሰማችሁም። |
እግዚአብሔርም፥ “ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ለአባቶቻችሁም እንዳዘዝሁት፥ በባሪያዎቼ በነቢያት የላክሁላችሁን ትእዛዜንና ሥርዐቴን፥ ሕጌንም ሁሉ ጠብቁ” ብሎ በነቢዩ ሁሉና በባለ ራእዩ አፍ ሁሉ በእስራኤልና በይሁዳ መሰከረ።
የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን እጅ፥ ከግብፅ ምድር ያወጣቸውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን በድለው ነበርና፥ ሌሎችንም አማልክት አምልከው ነበርና፤
ወደ ሕግህም ትመልሳቸው ዘንድ አስመሰከርህባቸው፤ ነገር ግን አልሰሙህም፤ ሰውም ባደረገው ጊዜ በሕይወት የሚኖርበትን ትእዛዝህንና ፍርድህን ተላለፉ፤ ጀርባቸውን ሰጡ፤ አንገታቸውንም አደነደኑ፤ አልሰሙምም።
በመካከልህ ወጥመድ እንዳይሆኑብህ አንተ በምትገባበት ምድር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የአሕዛብን መንገድ አትማሩ፤ ከሰማይ ምልክትም አትፍሩ፤ አሕዛብ ከእነርሱ የተነሣ ይፈራሉና።
እነርሱ ግን አልሰሙም፤ ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም፤ እንዳይሰሙና ተግሣጼን እንዳይቀበሉም ከአባቶቻቸው ይልቅ አንገታቸውን አደነደኑ።”
በአምላክሽ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፅሽ፥ መንገድሽንም ከለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች ለእንግዶች እንደ ዘረጋሽ፥ ቃሌንም እንዳልሰማሽ ኀጢአትሽን ብቻ ዕወቂ ይላል እግዚአብሔር።
ከትንሽነታችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኛና አባቶቻችን በአምላካችን በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ሠርተናልና፥ የአምላካችንንም የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማንምና በእፍረታችን ተኝተናል፤ ውርደታችንም ሸፍኖናል።”
እኔም ዛሬ ነግሬአችኋለሁ፤ ወደ እናንተም በላከኝ ነገር ሁሉ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማችሁም።
የቃርሔም ልጅ ዮሐናን፥ የጭፍራ አለቆችም ሁሉ፥ ሕዝቡም ሁሉ በይሁዳ ምድር ይቀመጡ ዘንድ የእግዚአብሔርን ቃል አልሰሙም።
ነገር ግን ሁሉም የወንጌልን ትምህርት የሰሙ አይደለም፤ ኢሳይያስም፥ “አቤቱ፥ ምስክርነታችንንስ ማን አመነ? የእግዚአብሔርስ ክንዱ ለማን ተገለጠ?” ብሎአልና።
እግዚአብሔርን ታመልኩ ዘንድ ባትወድዱ ግን፥ አባቶቻችሁ በወንዝ ማዶ ሳሉ ያመለኩአቸውን አማልክት፥ ወይም በምድራቸው ያላችሁባቸውን የአሞሬዎናውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ፥ የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን፤ እርሱ ቅዱስ ነውና።”
እናንተም በዚች ምድር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን አታድርጉ፤ ለአማልክቶቻቸውም አትስገዱላቸው፤ ምስሎቻቸውንም ስበሩ፤ መሠዊያቸውንም አፍርሱ አልሁ። እናንተ ግን ቃሌን አልሰማችሁም፤ ይህንስ ለምን አደረጋችሁ?
ከግብፃውያንም እጅ ከሚጋፉአችሁም ሁሉ እጅ አዳንኋችሁ፤ ከፊታችሁም አሳደድኋቸው፤ ሀገራቸውንም ሰጠኋችሁ፤