መሳፍንት 21:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፥ “አቤቱ፥ የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ ዛሬ ከእስራኤል አንድ ነገድ መታጣቱ፥ ስለምን ይህ በእስራኤል ላይ ሆነ?” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አሉ፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ ለምን በእስራኤል ላይ ሆነ? ዛሬ ከእስራኤል አንድ ነገድ እንዴት ይታጣ?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም አሉ፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ ሆይ፤ ይህ ለምን በእስራኤል ላይ ሆነ? ዛሬ ከእስራኤል አንድ ነገድ እንዴት ይታጣ?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም፦ አቤቱ፥ የእስራኤል አምላክ ሆይ! ዛሬ ከእስራኤል አንድ ነገድ መታጣቱ፥ ስለምን ይህ በእስራኤል ላይ ሆነ? አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ አቤቱ፥ የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ ዛሬ ከእስራኤል አንድ ነገድ መታጣቱ፥ ስለ ምን ይህ በእስራኤል ላይ ሆነ? አሉ። |
አቤቱ፥ ከመንገድህ ለምን አሳትኸን? እንዳንፈራህም ልባችንን ለምን አጸናህብን? ስለ ባሪያዎችህ ስለ ርስትህ ነገዶች ተመለስ፤
አቤቱ! ከአንተ ጋር በተምዋገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአንተ ጋር ስለ ፍርድ ልናገር። የኀጢአተኞች መንገድ ስለ ምን ይቀናል? በደልንስ የሚያደርጉ ሁሉ ስለ ምን ደስ ይላቸዋል?
አሕዛብ ሁሉ እግዚአብሔር በዚህች ምድር ስለ ምን እንደዚህ አደረገ? ይህስ የቍጣው ታላቅ መቅሠፍት ምንድን ነው? ይላሉ።
ሕዝቡም ወደ ቤቴል መጥተው በዚያ በእግዚአብሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ ተቀመጡ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው ጽኑዕ ልቅሶ አለቀሱ።