Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 21:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ሕዝ​ቡም ወደ ቤቴል መጥ​ተው በዚያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ ተቀ​መጡ፤ ድም​ፃ​ቸ​ው​ንም ከፍ አድ​ር​ገው ጽኑዕ ልቅሶ አለ​ቀሱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ሕዝቡ ወደ ቤቴል ሄደው በዚያም እስከ ማታ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት ተቀመጡ፤ ድምፃቸውንም ከፍ በማድረግ አምርረው አለቀሱ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ሕዝቡ ወደ ቤቴል ሄደው በዚያም እስከ ማታ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት ተቀመጡ፤ ድምፃቸውንም ከፍ በማድረግ አምርረው አለቀሱ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እስራኤላውያን ወደ ቤትኤል መጥተው በእግዚአብሔር ፊት እስከ ማታ ተቀምጠው ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ሕዝቡም ወደ ቤቴል መጥተው በዚያ በእግዚአብሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ ተቀመጡ፥ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው ጽኑ ልቅሶ አለቀሱ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 21:2
10 Referencias Cruzadas  

ዔሳ​ውም አባ​ቱን ይስ​ሐ​ቅን አለው፥ “አባቴ ሆይ፥ በረ​ከ​ትህ አን​ዲት ብቻ ናትን? አባቴ ሆይ፥ እኔ​ንም ደግሞ ባር​ከኝ።” ዔሳ​ውም ጮሆ አለ​ቀሰ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በሴሎ ተሰ​በ​ሰቡ፤ በዚ​ያም የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ተከሉ፤ ምድ​ሩም ጸጥ ብሎ ተገ​ዛ​ላ​ቸው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ይህን ቃል ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ በተ​ና​ገረ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ድም​ፃ​ቸ​ውን አን​ሥ​ተው አለ​ቀሱ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተነ​ሥ​ተው ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም፥ “የብ​ን​ያ​ምን ልጆች ለመ​ው​ጋት መሪ ሆኖ ማን ይው​ጣ​ልን?” ብለው ጠየ​ቁት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ይሁዳ መሪ ይሁን” አለ፤


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወጥ​ተው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ አለ​ቀሱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም፥ “ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ከብ​ን​ያም ልጆች ጋር ለመ​ዋ​ጋት ዳግ​መኛ እን​ቀ​ር​ባ​ለን?” ብለው ጠየቁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም “በእ​ነ​ርሱ ላይ ውጡ” አለ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ሕዝ​ቡም ሁሉ ወጥ​ተው ወደ ቤቴል መጡ፤ አለ​ቀ​ሱም፤ በዚ​ያም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተቀ​መጡ፤ በዚ​ያም ቀን እስከ ማታ ድረስ ጾሙ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ትን አቀ​ረቡ።


በኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓድ በሚ​ኖሩ መካ​ከ​ልም ወንድ ያላ​ወቁ አራት መቶ ቆነ​ጃ​ጅት ደና​ግ​ልን አገኙ፤ በከ​ነ​ዓ​ንም ሀገር ወዳ​ለ​ችው ወደ ሴሎ ወደ ሰፈሩ አመ​ጡ​አ​ቸው።


እነ​ር​ሱም፥ “አቤቱ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ ዛሬ ከእ​ስ​ራ​ኤል አንድ ነገድ መታ​ጣቱ፥ ስለ​ምን ይህ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ሆነ?” አሉ።


መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ቹም ሳኦል ወዳ​ለ​በት ወደ ገባ​ዖን መጥ​ተው ይህን ነገር በሕ​ዝቡ ጆሮ ተና​ገሩ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ድም​ፃ​ቸ​ውን ከፍ አድ​ር​ገው አለ​ቀሱ።


ዳዊ​ትና ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ሕዝብ ድም​ፃ​ቸ​ውን ከፍ አድ​ር​ገው ለማ​ል​ቀስ ኀይል እስ​ኪ​ያጡ ድረስ አለ​ቀሱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos