ወደ ምድረ በዳም ወጡ፤ ወደ ኬብሮንም ደረሱ፤ በዚያም የዔናቅ ዘሮች አኪማን፥ ሴሲ፥ ተላሚ ነበሩ። ኬብሮንም በግብፅ ካለችው ከጣኔዎስ ከተማ በፊት ሰባት ዓመታት ተሠርታ ነበር።
መሳፍንት 1:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም እንደ ተናገረ ለካሌብ ኬብሮንን ሰጡት፤ ከዚያም ሠላሳ ከተሞችን ወረሰ፤ ከዚያም ሦስቱን የዔናቅ ልጆች አስወገዳቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ ባዘዘው መሠረት ኬብሮን ለካሌብ ተሰጠች፤ እርሱም ሦስቱን የዔናቅ ልጆች ከውስጧ አሳደደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም እንደ ተናገረው ኬብሮን ለካሌብ ተሰጠች፤ እርሱም ሦስቱን የዐናቅ ልጆች ከውስጧ አሳደደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ ባዘዘው መሠረት ኬብሮን ለካሌብ ተሰጠ፤ ርሱም ሦስቱን የዐናቅ ጐሣዎች ከዚያ አስወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም እንደ ተናገረ ለካሌብ ኬብሮንን ሰጡት፥ ከዚያም ሦስቱን የዔናቅ ልጆች አወጣ። |
ወደ ምድረ በዳም ወጡ፤ ወደ ኬብሮንም ደረሱ፤ በዚያም የዔናቅ ዘሮች አኪማን፥ ሴሲ፥ ተላሚ ነበሩ። ኬብሮንም በግብፅ ካለችው ከጣኔዎስ ከተማ በፊት ሰባት ዓመታት ተሠርታ ነበር።
ወዳጄ ካሌብ ግን ሌላ መንፈስ በእርሱ ላይ ስለ ሆነና ስለ ተከተለኝ እርሱ ወደ ገባባት ምድር አገባዋለሁ፤ ዘሩም ይወርሳታል።
ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ በስተቀር፥ እርሱ ግን ያያታል፤ እግዚአብሔርን ፈጽሞ ተከትሎአልና የረገጣትን ምድር ለእርሱ፥ ለልጆቹም እሰጣለሁ።
በዚያ ጊዜም ኢያሱ ሄደ፤ በተራራማውም ሀገር የሚኖሩ ኤናቃውያንን ከኬብሮንና ከዳቤር፥ ከአናቦትም፥ ከእስራኤልም ተራራ ሁሉ፥ ከይሁዳም ተራራ ሁሉ አጠፋቸው፤ ኢያሱም ከከተሞቻቸው ጋር ፈጽሞ አጠፋቸው።
የኬብሮንም ስም አስቀድሞ የአርቦቅ ከተማ ትባል ነበር፤ እርስዋም የዔናቃውያን ዋና ከተማ ነበረች። ምድሪቱም ከውጊያ ዐረፈች።
ይሁዳም በኬብሮን ወደሚኖሩ ከነዓናውያን ሄደ። የኬብሮንም ሰዎች ወጥተው ተቀበሉት፤ የኬብሮንም ስም አስቀድሞ ቂርያታርቦቅሴፌር ነበረ። የኤናቅንም ትውልድ ሴሲንና አኪማምን፥ ተለሜንንም ገደሉአቸው።