ይሁዳ 1:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኀጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በሴሰኝነት ይለውጣሉ፤ ብቻውን ንጉሣችንንና ጌታችንንም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከረዥም ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንድ ሰዎች ሾልከው ወደ እናንተ ገብተዋልና፤ እነርሱ ፈሪሀ እግዚአብሔር የሌላቸው፣ የአምላካችንን ጸጋ በርኩሰት የሚለውጡና እርሱ ብቻ ልዑል ገዣችንና ጌታችን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚክዱ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አስቀድሞ ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኃጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በዝሙት ይለውጣሉ፤ ብቸኛ ንጉሣችንና ጌታችን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚፈረድባቸው መሆኑ ከብዙ ጊዜ በፊት የተጻፈባቸው አንዳንድ ሰዎች ወደ እናንተ ሾልከው ገብተዋል፤ እነርሱ የአምላካችንን ጸጋ በስድነት የሚለውጡ እግዚአብሔርን የማያመልኩ ናቸው፤ እርሱ ብቻ ገዢአችንና ጌታችን የሆነን ኢየሱስ ክርስቶስንም ይክዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኃጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በሴሰኝነት ይለውጣሉ ንጉሣችንንና ጌታችንንም ብቻውን ያለውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ። |
ምስጉን ነው፥ በዝንጉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኀጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ ሰው።
ብቻህን እውነተኛ አምላክ የሆንህ አንተን፥ የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘለዓለም ሕይወት ናት።
በደረሰ ጊዜም የእግዚአብሔርን ጸጋ አየና ደስ አለው፤ በፍጹም ልባቸውም በእግዚአብሔር ጸንተው ይኖሩ ዘንድ መከራቸው።
ያላዘዝናቸው ሰዎች ከእኛ ወጥተው፦ ‘ትገዘሩ ዘንድና የኦሪትንም ሕግ ትጠብቁ ዘንድ ይገባችኋል’ ብለው በነገር እንደ አወኩአችሁና ልባችሁን እንደ አናወጡት ሰምተናል።
ይኸውም ባሪያዎች ያደርጉን ዘንድ በኢየሱስ ክርስቶስ ያገኘናትን ነጻነት ሊሰልሉ በስውር ወደ እኛ የገቡ ሐሰተኞች መምህራንን ደስ አይበላቸው ብዬ ነው።
ወንድሞች ሆይ፥ እናንተስ ለነጻነት ተጠርታችኋል፤ ነገር ግን በሥጋችሁ ፈቃድ ለነጻነታችሁ ምክንያት አታድርጉላት፤ ለወንድሞቻችሁም በፍቅር ተገዙ።
እንግዲህ በሽንገላቸው ያስቱ ዘንድ በሚተናኰሉ ሰዎች ተንኰል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ ወዲያና ወዲህ እየተፍገመገምንና እየተንሳፈፍን ሕፃናት አንሁን።
ወደ ቤቶች ሾልከው እየገቡ ኀጢአታቸው የተከመረባቸውን በልዩ ልዩ ምኞትም የሚወሰዱትን ሁልጊዜም እየተማሩ እውነትን ወደ ማወቅ ሊደርሱ ከቶ የማይችሉትን ሞኞችን ሴቶች የሚማርኩ፥ ከእነዚህ ዘንድ ናቸውና።
ጻድቅ ሎጥም በመካከላቸው ሲኖር እያየና እየሰማ ዕለት ዕለት በዐመፀኛ ሥራቸው ጻድቅ ነፍሱን አስጨንቆ ነበርና በዐመፀኞች ሴሰኛ ኑሮ የተገፋውን ያን ጻድቅ ካዳነ፥
አሁን ያሉ ሰማያትና ምድር ግን እግዚአብሔርን የማያመልኩት ሰዎች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ተጠብቀው በዚያ ቃል ለእሳት ቀርተዋል።