Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 15:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ያላ​ዘ​ዝ​ና​ቸው ሰዎች ከእኛ ወጥ​ተው፦ ‘ትገ​ዘሩ ዘን​ድና የኦ​ሪ​ት​ንም ሕግ ትጠ​ብቁ ዘንድ ይገ​ባ​ች​ኋል’ ብለው በነ​ገር እንደ አወ​ኩ​አ​ች​ሁና ልባ​ች​ሁን እንደ አና​ወ​ጡት ሰም​ተ​ናል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 አንዳንድ ሰዎች ያለ እኛ ፈቃድ ከእኛ ዘንድ ወጥተው በንግግራቸው ልባችሁን እንዳወኩና እንዳናወጧችሁ ሰምተናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ያላዘዝናቸው ሰዎች ከእኛ ወጥተው ‘ትገረዙ ዘንድና ሕግን ትጠብቁ ዘንድ ይገባችኋል፤’ ብለው ልባችሁን እያወኩ በቃል እንዳናወጡአችሁ ስለ ሰማን፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ከእኛ መካከል አንዳንድ ሰዎች እኛ ሳናዛቸው ወደ እናንተ መጥተው በነገሩአችሁ ቃል እንዳስቸገሩአችሁና ግራ እንዳጋቡአችሁ ሰምተናል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ያላዘዝናቸው ሰዎች ከእኛ ወጥተው፦ ‘ትገረዙ ዘንድና ሕግን ትጠብቁ ዘንድ ይገባችኋል’ ብለው ልባችሁን እያወኩ በቃል እንዳናወጡአችሁ ስለ ሰማን፥

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 15:24
12 Referencias Cruzadas  

ኀያል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ሩ​ላ​ች​ሁን የነ​ቢ​ያ​ትን ቃል አት​ስሙ፤ ከን​ቱ​ነ​ትን ያስ​ተ​ም​ሩ​አ​ች​ኋል፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ ሳይ​ሆን ከገዛ ልባ​ቸው የወ​ጣ​ውን ራእይ ይና​ገ​ራሉ።


ከይ​ሁዳ ሀገ​ርም የወ​ረዱ ሰዎች፥ “እንደ ሙሴ ሕግ ካል​ተ​ገ​ዘ​ራ​ችሁ ልት​ድኑ አት​ች​ሉም” እያሉ ወን​ድ​ሞ​ችን ያስ​ተ​ምሩ ነበር።


እርሱ ግን ሌላ አይ​ደ​ለም፤ የሚ​ያ​ው​ኳ​ችሁ ከክ​ር​ስ​ቶ​ስም ወን​ጌል ሊያ​ጣ​ምሙ የሚ​ወዱ አሉ እንጂ።


እኔ ሌላ እን​ዳ​ታ​ስቡ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አም​ኛ​ችሁ ነበር፤ የሚ​ያ​ው​ካ​ችሁ ግን የሆ​ነው ቢሆን ፍዳ​ውን ይሸ​ከ​ማል።


የሚ​ያ​ው​ኩ​አ​ች​ሁም ሊለዩ ይገ​ባል።


በኦ​ሪት ልት​ጸ​ድቁ የም​ት​ፈ​ልጉ እና​ንተ ከክ​ር​ስ​ቶስ ተለ​ይ​ታ​ችሁ ከጸ​ጋዉ ወድ​ቃ​ች​ኋል።


ይህን አሳስባቸው፤ በቃልም እንዳይጣሉ በእግዚአብሔር ፊት ምከራቸው፤ ይህ ምንም የማይረባ የሚሰሙትንም የሚያፈርስ ነውና።


ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ወጡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos