አብራምም ሚስቱን ሦራን፥ “እነሆ፥ አገልጋይሽ በእጅሽ ናት፤ እንደ ወደድሽ አድርጊባት” አላት። ሦራም አጋርን አሠቃየቻት፤ ከእርስዋም ኰበለለች።
ኢያሱ 9:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም እነሆ፥ በእጃችሁ ውስጥ ነን፤ እንደ ወደዳችሁና ደስ እንደሚላችሁ አድርጉብን” አሉት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ አሁን በእጅህ ውስጥ ነን፤ በጎና ትክክል መስሎ የታየህን ነገር ሁሉ አድርግብን።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ አሁን፥ እነሆ፥ በእጅህ ውስጥ ነን፤ ለዓይንህም መልካምና ቅን የመሰለውን ነገር አድርግብን።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ፥ አሁን በእናንተ ሥልጣን ሥር ነን፤ መልካም መስሎ የታየህን ሁሉ አድርግብን።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም፥ እነሆ፥ በእጅህ ውስጥ ነን፥ ለዓይንህም መልካምና ቅን የመሰለውን ነገር አድርግብን አሉት። |
አብራምም ሚስቱን ሦራን፥ “እነሆ፥ አገልጋይሽ በእጅሽ ናት፤ እንደ ወደድሽ አድርጊባት” አላት። ሦራም አጋርን አሠቃየቻት፤ ከእርስዋም ኰበለለች።
ዳዊትም ጋድን፥ “በሁሉም እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ በሰው እጅ ከምወድቅ ይልቅ ምሕረቱ ብዙ ነውና በእግዚአብሔር እጅ መውደቅ ይሻለኛል” አለው።
የአክአብም የቤቱ አለቆች፥ የከተማዪቱም አለቆች፥ ሽማግሌዎቹና ልጆቹንም የሚያሳድጉ፥ “እኛ አገልጋዮችህ ነን፤ ያዘዝኸንንም ሁሉ እናደርጋለን፤ የምናነግሠው ሰው የለም፤ የምትወድደውን አድርግ” ብለው ወደ ኢዩ ላኩ።
በሕዝቤ ላይ ተቈጥቼ ነበር፤ ርስቴንም አረከስሽ፤ በእጅሽም አሳልፌ ሰጠኋቸው፤ ለሽማግሌዎቻቸው አልራራሽም፤ ቀንበራቸውንም እጅግ አክብደሻል።
የእስራኤልም ልጆች እግዚአብሔርን፥ “እኛ ኀጢአትን ሠርተናል፤ አንተ በፊትህ ደስ የሚያሰኝህን አድርግብን፤ ዛሬ ግን እባክህ አድነን” አሉት።
ጌዴዎንም ወደ ሱኮት አለቆች መጥቶ፥ “ለደከሙት ሰዎችህ እህል እንሰጥ ዘንድ የዛብሄልና የስልማና እጅ አሁን በእጅህ ነውን? ብላችሁ የተላገዳችሁብኝ፥ ዛብሄልና ስልማና እነሆ፥” አለ።
ሳሙኤልም ነገሩን ሁሉ ነገረው፤ አንዳችም አልሸሸገውም። ዔሊም፥ “እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ ደስ ያሰኘውን ያድርግ” አለ።