“እኔ ጥንቱን እንደ ሠራሁት፥ ቀድሞውንም እንዳደረግሁት አልሰማህምን? አሁንም የተመሸጉትን ከተሞች የፍርስራሽ ክምር እስኪሆኑ ድረስ እንድታፈርስ አደረግሁህ።
ኢያሱ 8:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም ከተማዋን በእሳት አቃጠላት፤ ዐመድም ሆነች፤ እስከ ዛሬም ድረስ ለዘለዓለሙ የሚኖርባት እንዳይኖር አደረጋት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ኢያሱ ጋይን አቃጠላት፤ እስከ ዛሬ እንደሚታየውም ለዘላለም የዐመድ ቍልልና ባድማ አደረጋት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም ጋይን አቃጠላት፥ እስከ ዛሬም ድረስ የፍርስራሽ ክምር ለዘለዓለም አደረጋት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢያሱ የዐይን ከተማ በማቃጠል ለዘለዓለም ፍርስራሽ አድርጎ ተዋት፤ እስከ አሁንም ድረስ በዚህ ዐይነት ትገኛለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም ጋይን አቃጠላት፥ እስከ ዛሬም ድረስ ድብድባና በረሃ ለዘላለም አደረጋት። |
“እኔ ጥንቱን እንደ ሠራሁት፥ ቀድሞውንም እንዳደረግሁት አልሰማህምን? አሁንም የተመሸጉትን ከተሞች የፍርስራሽ ክምር እስኪሆኑ ድረስ እንድታፈርስ አደረግሁህ።
ከተሞችን ትቢያ አደረግህ፤ የተመሸጉ ከተሞችን፥ የኃጥኣንንም መሠረት አፈረስህ፤ ከተሞቻቸውም ለዘለዓለም አይሠሩም።
ስለዚህ እነሆ በአሞን ልጆች ከተማ በራባት ላይ የሰልፍ ውካታን የማሰማበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ለጥፋትም ትሆናለች፥ መንደሮችዋም በእሳት ይቃጠላሉ፤ እስራኤልም የወረሱትን ይወርሳል፥ ይላል እግዚአብሔር።
ኢየሩሳሌምንም የፍርስራሽ ክምር፥ የቀበሮም ማደሪያ አደርጋታለሁ፤ የይሁዳንም ከተሞች ሰው እንዳይቀመጥባቸው አጠፋቸዋለሁ።
ዕቃዋንም ሁሉ ወደ አደባባይዋ ትሰበስባለህ፤ ከተማይቱንም፥ ዕቃዋንም ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት በእሳት ፈጽመህ ታቃጥላለህ፤ ለዘለዓለምም ወና ትሆናለች፤ ደግሞም አትሠራም።
የእግዚአብሔር የመቅሠፍቱ ቍጣ ይመለስ ዘንድ፥ ለአባቶችህም እንደ ማለላቸው ይምርህ ዘንድ፥ ይራራልህም ዘንድ፥ ያበዛህም ዘንድ፥ ርጉም ከሆነው አንዳች ነገር በእጅህ አትንካ።
ኢያሱም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግሮች በቆሙበት ስፍራ በዮርዳኖስ መካከል ሌሎች ዐሥራ ሁለት ድንጋዮችን አቆመ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ።
የጋይንም ንጉሥ በዝግባ ዛፍ ላይ ሰቀለው፤ እስከ ማታም ድረስ በዛፉ ላይ ቈየ። ፀሐይም በገባች ጊዜ ኢያሱ ያወርዱት ዘንድ አዘዘ፤ ከዛፉም አወረዱት፤ በከተማዪቱም በር አደባባይ ጣሉት፤ በላዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለውን ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩበት።