La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 8:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የጋ​ይም ሰዎች ወደ ኋላ​ቸው ዞረው በተ​መ​ለ​ከቱ ጊዜ የከ​ተ​ማ​ዪቱ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፤ ወዲ​ህና ወዲያ መሸሽ አል​ቻ​ሉም፤ ወደ ምድረ በዳም የሸሹ ሕዝብ በሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​አ​ቸው ላይ ተመ​ለሱ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የጋይ ሰዎች ወደ ኋላ ዞረው ሲመለከቱ የከተማዪቱ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፤ ወደ ምድረ በዳ ይሸሹ የነበሩት እስራኤላውያን ፊታቸውን ስላዞሩባቸውም፣ በየትኛውም በኩል ማምለጫ መንገድ አልነበራቸውም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የጋይም ሰዎች ወደ ኋላቸው ዞረው የከተማይቱ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፤ ወደ ምድረ በዳም የሸሸው ሕዝብ በሚያሳድዱአቸው ላይ ስለ ተመለሱ ወዲህና ወዲያም መሸሽ አልቻሉም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የዐይ ከተማ ሰዎችም ወደ ኋላ መለስ ብለው ባዩ ጊዜ የከተማይቱ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፤ ወደ ምድረ በዳ የሸሹት እስራኤላውያን በአሳዳጆቻቸው ላይ ስለ ተመለሱባቸው፥ በየትም በኩል ለማምለጥ አልቻሉም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የጋይም ሰዎች ወደ ኋላቸው ዞረው የከተማይቱ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፥ ወዲህና ወዲያም መሸሽ አልቻሉም፥ ወደ ምድረ በዳም የሸሹ ሕዝብ በሚያሳድዱአቸው ላይ ተመለሱ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 8:20
14 Referencias Cruzadas  

ወደ ሰዶ​ምና ገሞራ፥ ወደ አው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ዋም ሁሉ ተመ​ለ​ከተ፤ እነ​ሆም፥ ነበ​ል​ባል ከም​ድር እንደ ምድጃ ጢስ ሲወጣ አየ።


የኃ​ጥ​ኣን መድ​ኀ​ኒ​ታ​ቸው ታል​ቃ​ለች። ተስ​ፋ​ቸ​ው​ንም ያጣሉ፥ የዝ​ን​ጉ​ዎች ዐይ​ኖ​ችም ይጠ​ፋሉ።”


የድ​ሮ​ውን ዘመን ዐሰ​ብሁ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙን ዓመ​ታት ዐሰ​ብሁ፤ አነ​በ​ብ​ኹም፤


ጢሱም ወደ​ላይ ይወ​ጣል፤ ከት​ው​ልድ እስከ ትው​ል​ድም ድረስ ባድማ ሆና ትኖ​ራ​ለች፤ ለብዙ ዘመ​ና​ትም ትጠ​ፋ​ለች።


የተ​ደ​በ​ቁ​ትም ፈጥ​ነው ከስ​ፍ​ራ​ቸው ተነሡ፤ ኢያ​ሱም እጁን በዘ​ረጋ ጊዜ ወጡ፤ ወደ ከተ​ማ​ዋም ገብ​ተው ያዙ​አት፤ ፈጥ​ነ​ውም በእ​ሳት አቃ​ጠ​ሉ​አት።


ኢያሱ፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ተደ​ብ​ቀው የነ​በ​ሩት ከተ​ማ​ዪ​ቱን እንደ ያዙ፥ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ ባዩ ጊዜ ወደ​ኋላ ተመ​ል​ሰው የጋ​ይን ሰዎች ገደ​ሉ​አ​ቸው።


ከእርስዋም ጋር የሴሰኑና የተቀማጠሉ የምድር ነገሥታት የመቃጠልዋን ጢስ ሲያዩ ስለ እርስዋ እየጮሁ እያሉ ያለቅሳሉ፤


ደግመውም “ሃሌ ሉያ! ጢስዋም ለዘላለም እስከ ዘላለም ይወጣል፤” አሉ።


የተ​ደ​በ​ቁ​ትም ሰዎች ከከ​ተ​ማው ብዙ ጢስ እንደ ደመና እን​ዲ​ያ​ስ​ነሡ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና በተ​ደ​በ​ቁት ሰዎች መካ​ከል ምል​ክት ተደ​ርጎ ነበር።


ምል​ክ​ቱም በጢሱ ዐምድ ከከ​ተ​ማው ሊወጣ በጀ​መረ ጊዜ ብን​ያ​ማ​ው​ያን ወደ​ኋ​ላ​ቸው ተመ​ለ​ከቱ፤ እነ​ሆም፥ የሞላ ከተ​ማው ጥፋት ወደ ሰማይ ወጣ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተመ​ለሱ፤ የብ​ን​ያ​ምም ሰዎች ተሸ​በሩ፤ ክፉ ነገር እንደ ደረ​ሰ​ባ​ቸ​ውም አዩ።